1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሕወሐት ላይ የሚሰነዘረዉ ወቀሳ፦ የኢሕአዴግና የመንግስት አቋም

ሐሙስ፣ የካቲት 25 2002

ቢቢሲ የቀድሞ የሕወሐት ባለሥልጣናትንና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ በ1977 ግድም በረሐብ ለተጎዳዉ ሕዝብ የተሰጠ የገንዘብ ርዳታን የሕዉሐት መሪዎች ጠመንጃ ገዝተዉበታል በማለት ዘግቦ ነበር

https://p.dw.com/p/MJrm
የ1977ተረጂዎች ትግራይ

ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) በነፍጥ በሚታገልበት ወቅት በረሐብ ለተጎዳዉ ሕዝብ የተላከዉን የዉጪ ርዳታ ለጦር መሳሪያ መግዢያ አዉሎታል የሚለዉን ክስ ሕዋሐት አባል የሆነበት የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ አስተባባለ።የብሪታንያዉ ማሠራጪያ ጣቢያ ቢቢሲ የቀድሞ የሕወሐት ባለሥልጣናትንና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ በ1977 ግድም በረሐብ ለተጎዳዉ ሕዝብ የተሰጠ የገንዘብ ርዳታን የሕዉሐት መሪዎች ጠመንጃ ገዝተዉበታል በማለት ዘግቦ ነበር።የኢሕአዴግ የሕዝብና የዉጪ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸዉ ዛሬ እንዳሉት ግን ዘገባዉ መሠረተ ቢስ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም ዘገባዉን አስተባብሏል።ነጋሽ መሐመድ የኮሚኒኬሽን ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማልን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ