1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሐረሩ ግጭት የተጠረጠሩ 87 ሰዎች ታሰሩ 

ሰኞ፣ ጥር 18 2012

በተለያየ መንገድ በግጭቱ ተሳትፈዋል ተብለው በተጠረጠሩት በእነዚሁ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለዶቼቬለ አስታውቋል። በግጭቱ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን፤ ሰላማዊ ሰዎችና የፀጥታ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ተሽከርካሪዎችም ተዘርፈው እንደነበር ፖሊስ ተናግሯል።

https://p.dw.com/p/3Wsnh
Hyänen Äthiopien
ምስል Reuters/T.Negeri

ፖሊስ ግጭቱን ለመከላከል ኃይል ተጠቅሟል አድሎም ፈጽሟል መባሉን አስተባብሏል

አንድ ሰው በሞተበት እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በቆሰሉበት የዕለተ ጥምቀት የሐረር ግጭት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 87 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሐረሪ ክልል ፖሊስ አስታወቀ። በተለያየ መንገድ በግጭቱ ተሳትፈዋል ተብለው በተጠረጠሩት በእነዚሁ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለዶቼቬለ አስታውቋል። በግጭቱ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን፤ ሰላማዊ ሰዎችና የፀጥታ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ተሽከርካሪዎችም ተዘርፈው እንደነበር ፖሊስ ተናግሯል። ፖሊስ ግጭቱን ለመከላከል ኃይል ተጠቅሟል አድሎም ፈጽሟል መባሉን አስተባብሏል። 


መሳይ ተክሉ 


ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ