1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሀዋሳ የመታሸግ ዕጣ የገጠማቸው ፋብሪካዎች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 27 2002

በሀዋሳ 10 ሺህ ኩንታል የእርዳታ እህል በመጋዘናቸው የተገኘባቸው ፋብሪካዎች ታሸጉ

https://p.dw.com/p/Ob7l
ስንዴምስል DW-TV

ኢትዮዽያ ፤ማሽላና በቆሎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የመጀመሯ ዜና ሲሰማ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የአውሮፓ ህብረት በቅርቡ 15 ሚሊዮን ዩሮ በድርቅ እና በርሀብ ለሚጎዱ ኢትዮጲያውያን እንዲውል፤ እርዳታ እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ በሀዋሳ ከተማ 10 ሺህ ኩንታል የእርዳታ ስንዴ በመጋዘናችሁ ተገኝቷል ተብለው፤ 10 ዱቄት ፋብሪካዎች ታሽገዋል። ፖሊስ እያጣራሁ ነው ይላል። ከተዘጋባቸው የዱቄት ፋብሪካ ባሌቤቶች አንደኛው ማሸጊያ ማዳበሪያው እንጂ ስንዴው የሀገር ውስጥ ነው ይላሉ። ልደት አበበ የሚመለከታቸውን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አሰናድታለች።