1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቆይታ ከአርቲስት ንብረት ገላዉ ጋር

እሑድ፣ ጥር 6 2010

የአገር ቤት የአነጋገር ለዛ ያላቸዉን ገፀ-ባህሪያት ወክሎ በመጫወት ይበልጡኑ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ላለፉት 20 አመታት በተለያዩ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎች እንዲሁም በመድረክ ቲያትሮች በርካታ ገፀ-ባህሪትን ወክሎ ሲተወን ቆይቷል። ድራማዎችን ይፅፋል። ያዘጋጃልም። በግል ጋዜጣና በመጽሄቶች ላይም በሪፓርተርነትና በአዘጋጅነት መስራቱን ይናገራል።

https://p.dw.com/p/2qlBY
Nibret Gelaw äthiopischer Künstler
ምስል Privat

Unterhaltung 14.1.2017/ Artist Nibret Gelaw/ - MP3-Stereo

የአገር ቤት የአነጋገር ለዛ ያላቸዉን ገፀ-ባህሪያት ወክሎ በመጫወት ይበልጡኑ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ላለፉት 20 አመታት በተለያዩ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎች እንዲሁም በመድረክ ቲያትሮች  በርካታ ገፀ-ባህሪትን ወክሎ ሲተወን ቆይቷል። ድራማዎችን ይፅፋል። ያዘጋጃልም። በግል ጋዜጣና በመጽሄቶች ላይም በሪፓርተርነትና  በአዘጋጅነት መስራቱን ይናገራል። በተለይ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ በርካታ ፅሁፎችን ማቅረቡንም አጫዉቶናል።ለዚሁ ስራዉ ይረዳዉ ዘንድም የምልክት ቋንቋ እስከመማር ደርሷል። «እከ» በሚለዉ የገፀ-ባህሪ ስሙ ብዙዎች ያዉቁታል። የዛሬዉ የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን የጥበብ ሰዉ ንብረት ገላዉ ነው። ሙሉ ዝግጅቱን ለማድመጥ የድምጹን ማዕቀፉን ይጫኑ።

ፀሀይ ጫኔ

አርያም ተክሌ