1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈዉ ዉሳኔ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2005

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገር ዉስጥ የሚገኘዉ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአንድ ሳምንት በላይ ያካሄደዉን ዓመታዊ ጉባኤ ትናንት አጠናቋል። ሲኖዶሱ በዝግ ያካሄደዉን ስብሰባ ትናንት ሲያጠናቅቅ ባወጣዉ መግለጫ፤

https://p.dw.com/p/16bBe
ምስል DW

17 ነጥቦችን በመጥቀስ በቀጣይ እንዲከናወኑ ዉሳኔ ማሳለፉን አመልክቷል። ጥቅምት 11 ቀን 2005ዓ,ም በሥርዓተ ፀሎት የተጀመረዉ የቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት ዓመታዊ ጉባኤ ካለፉት ዓመታት አንፃር ብዙም መረጃዎች ሳይሾልኩበት በዝግ የተካሄደ መሆኑ ነዉ የሚነገረዉ። እንዲያም ሆኖ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘዉና በአራተኛዉ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከሚመራዉ ሲኖዶስ ጋ ስለተጀመረዉ የእርቀ ሰላም ጉዳይ፤ እንዲሁም ስለፓርቲያርክ ምርጫና የምርጫ ስርዓት አበክሮ እንደሚነጋገር መሰማቱ አልቀረም። ትናንት ሲኖዶሱ ጉባኤዉን ማጠናቀቁን ይፋ በማድረግ የሰጠዉ መግለጫም የተጠቀሱት ነጥቦች እዉነትም እንደተባለዉ ከዋነኞች መነጋገሪ ጉዳዮች ተርታ መሆናቸዉን ጉባኤዉ ሲጠናቀቅ የወጣዉ መግለጫ አመልክቷል። መግለጫዉ በስደት በሚገኙና ሀገር ዉስጥ ባሉት የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች መካከል የተጀመረዉን እርቀሰላም አስመልክቶ በጥቅሉ እንዲቀጥል ሲኖዶሱ ወስኗል ከማለት ያለፈ ነገር አላመለከተምና ይህን እንዲያብራሩልን አቡነ ሕዝቅኤልን ጠይቀናቸዋል፤

ሸዋዬ ከገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ