1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶሪያ በሠላምና ጦርነት መሐል

ሰኞ፣ ሚያዝያ 8 2004

የተኩስ አቁሙ ተጨማሪ ሕይወት እንዳይጠፋ መጠቅሙ አያከራክርም።እራሳቸዉን «የሶሪያ ወዳጆች» የሚሉ ሐይላትም አንዱን ደግፎ ሌላዉን ከማዉገዝ ይልቅ ተፋላሚዎች ለሰላም እንዲገዙ ካግባቡ በርግጥ የሶሪያ-የምድሩ ሳይሆን የሕዝቡ እዉነተኛ ወዳጅነታቸዉን

https://p.dw.com/p/14evw
REFILE - CORRECTING SPELLING COLONEL'S NAME Colonel Ahmed Himmiche (C), a member of a U.N. monitors team, speaks to the media at a hotel in Damascus April 16,2012. A United Nations advance observers' team arrived in the Syrian capital Damascus late Sunday to monitor the fragile cease-fire brokered by international envoy Kofi Annan, causing discussion from all circles in Syria. REUTERS/Khaled al- Hariri (SYRIA - Tags: CIVIL UNREST MILITARY POLITICS)
ታዛቢዎቹምስል Reuters

አረጋገጡ ማለት ነዉ። ሆምስ እሁድ።

የሶሪያዋ የግጭት ዉጊያ ማዕከል ሆምስ በርግጥ አላረፈችም።የኮፊ አናን የሠላም ዕቅድ፣የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔ ግን ሶሪያን የሚንጠዉን ዉጊያ ባያቆመዉ፣ ማቀዝቀዙ፣ የሕዝቧን ዕልቂት ባያስወግደዉ መቀነሱ፣አላነጋገረም።ተፋላሚዎች እንደተቆራቆሱ፥ለመጠፋፋት ለማጥፋት እንተደዛዛቱ፣ ያቀዘቀዙት ዉጊያ-ከመክሰሙ ይልቅ የመጋሙ ሥጋት ማየሉ እንጂ-ድቀቱ። የሪያድ ዶሐ ነገስታት፣ የአንካራ-ትሪፖሊ ገዢዎች የደማስቆ ጠላቶችን ለማስታጠቅ፣ እየፎከሩ፣ ዋሽግተን፣ብራስልሶች ፎካሪዎችን እንዳጃገኑ፥የባግዳድ፣ቴሕራን የሞስኮ-ቤጂንግ ገዢዎች ፎካሪ፣ አጃጋኞችን እንደተፃረሩ፣ ኒዮርክ ላይ የወሰኑት የሶሪያን ድቀት፣ የሕዝቧን እልቂት ለማስቆም መፈየዱ ነዉ አጠያያቂዉ።ላፍታ አብረን እንጠይቅ።

ተኩሱ ፀናም-ለነቆሰ ቆመ።ሐሙስ።የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤትም የታዛቢዎች ቡድን ለመላክ ወሰነ።

«የድምፁ ዉጤት እንደሚከተለዉ ነዉ።ረቂቅ ዉሳኔዉ አስራ-አምስት የድጋፍ ድምፅ አግኝቷል።ረቂቅ ዉሳኔዉ የሁለት ሺሕ አስራ-ሁለት ዉሳኔ ቁጥር 2042 በሚል ሥያሜ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።»

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርና የወቅቱ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሱዛን ራይስ።ቅዳሜ።የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በሶሪያ ጉዳይ ባንድ ድምፅ-ሲወስን ባለፉት አስራ-ሰወስት ወራት ዉስጥ የቅዳሜዉ የመጀመሪያዉ ነዉ።በዉሳኔዉ መሠረት ወደ ሶሪያ ከሚዘምቱት ሁለት መቶ ሐምሳ ታዛቢዎች ቀዳሚዎቹ ስድስቱ ትናንት ደማስቆ ገብተዋል።

ስድስት ወታደር-ምን ሊሰራ ምንስ ሊተክር ማሰኘቱ አልቀረም።የልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን ቃል አቀባይ አሕመድ ፈዉዚ መልስ አላቸዉ።«ብዙዎች ሥድስት ሰዎች ምን ማድረግ ይችላሉ?እንደሚሉ አዉቃለሁ።እኛ ግን ሰማያዊ መለዮ ለባሾች አንድ ሁለት አካባቢዎች መታየታቸዉ ዉጥረቱን ያረግበዋል ብለን እናምናለን።»

የታዛቢዉ ቡድን ቁጥር አነሰም በዛ ሐሙስ ድፍን ሶሪያ፥ ቅዳሜ ኒዮርክ፥ ትናንት ደግሞ ደማስቆ የሆነዉን ከሳምንታት በፊት ይሆናል ብሎ የጠበቀ ብዙም አልነበረም።ግን ሆነ። ተስፋ።

የሶሪያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወሊድ አል-ሙዓሊም ባለፈዉ ማክሰኞ ያሉትም መንግስታቸዉ የልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን እቅድ ከተቀበለበት ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ካለዉ ብዙም የተለየ አልነበረም።ከሐሙስ እስከዛሬ ደማስቆ ሥለሚሆነዉ ፍንጭ መስጠታቸዉ ግን አል«ጦራችንን (ከከተሞች) ማስወጣት ጀምረናል።ይሕን ቀና እርምጃ ብንወስድም የታጠቁ አሸባሪዎች የሚፈፅሙትን ጥቃት ማጠናከራቸዉና ማስፋፋታቸዉን እያየን ነዉ።»

ወዳጆች፥ የፍቅራቸዉ ጥብቀት ተነግሮ ሳያበቃ የጠላትነቻዉ ክረት በሚፈጋበት፣ የተገባ ቃል ባፍታ በንኖ ሌላ ቃል በሚገባበት፣ የታለመ፣ የታቀደዉ ተሰርዞ ያልታሰበ በሚፈፀምበት፣ ዉል፣ ስምምነት ከመፈረሙ ቅፅበት በሚሻርበት በዚያ ምድር የሆነዉን እንጂ የሚሆነዉን መናገር በርግጥ ሊያሳት ይችላል።መካከለኛዉ ምሥራቅ።

የሶሪያ መንግሥት ከደማስቆ፣ በተደጋጋሚ ያለዉንም «አለ ከማለት» ባለፍ ገቢር ያደርገዋል ብሎ ያመነ-ከነበረ እሱ በርግጥ ለጉደኛዉ ምድር የጉድ ነባር ፖለቲካዊ እዉነት፥ ለደማስቆ ሥርዓት ባሕሪም እንግዳ ነዉ ማለት ይቻላል።ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወሊድ ሙዓሊም ያሉትንም ተቃዋሚዎቻቸዉም ሆኑ ሌሎች ቢጠራጠሩ ወይም ባያምኑ አይፈረድባቸዉም። ሚንስትሩ ያሉትን ያሉበትን ሥፍራና ሁኔታ አለማጤን ግን አድም ዲፕሎማሲያዊ ስሕተት አለያም ፖለቲካዊ ቂልነት ወይም ወታደራዊ እብሪት ነዉ-የሚሆን።

የሶሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰኘዉ የተቃዋሚዎች ስብስብ ቃል አቀባይ ሎይ ሳፊ፣ የሶሪያዉን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል ቢጠራጠሩ ከዚያ ምድር ነባር እዉነት፥ ከደማስቆ ፖለቲከኞች ባሕሪ የሚጨለፍ አያሌ ምክንያት ሥላለቸዉ አያስወቅሳቸዉም።ቃል አቀባይ ሳፊ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ያሉትን ያሉት ሞስኮ፣ ከሩሲያዉ አቻቸዉ ከሰርጌይ ላቭሮቭ ጎን ተቀምጠዉ መሆኑን፣ ሙዓሊም ያሉትን ላቭሮቭ መድገማቸዉንም ያጤኑት አልመሰሉም።«ከወለድ ሙዓለም የምንሰማዉ ያዉ ዓለምን እያተለሉ መሆናቸዉን ነዉ።ጦራቸዉን ማስወጣታቸዉን ተናግረዋል።እንደ እዉነቱ ከሆነ ሐይላቸዉን ቦታ እየቀየሩ እያሰፈሩት ነዉ።ጦራቸዉን ወደሰፈሩ እንመልሳለን የሚሉትም ከምራቸዉ አይደለም።»

ቃል አቀባይ ሳፊ ሙዓሊምን ሲያጣጥሉ ላቭሮቭንም መጨፍለቃቸዉ፥ ደማስቆን ሲያወግዙ ከሞስኮም መላተማቸዉ መሆኑን አላጤኑትም።ተኩስ አቁም በመሠረቱ የተፋላሚ ወነገኖች እርምጃ ዉጤት ነዉ።ቃል አቀባይ ሳፊ ከተኩስ አቁም ተዋዋዮች እንደ አንደኛዉ ወገን ተወካይ ድርጅታቸዉ ለስምምነቱ መገዛት-አለመገዛቱን ገድፈዉ፣ ደማስቆን ከመጠርጠር አልፈዉ፣ ሙዓሊምን በቀጥታ ላቭሮቭን በተዘዋዋሪ ማዉገዛቸዉ ድርጅታቸዉ በገዳይ-ቀጣፊነት ከሚወነጅለዉ መንግሥት መለየቱን አጠያያቂ፣ ከድርጅታቸዉ ጀርባ ያሉት ሐይላት ለሶሪያ ሰላም መቆማቸዉን አጠራጣሪ ያደርገዋል።

ልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን ባለፈዉ ሮብ ሥለ ተኩስ አቁሙ ስምምነት መክሸፍ- አለመክሸፍ ለመናገር ጊዜዉ ገናነዉ ማለታቸዉ አልቀረም።«ዕቅዱ ተጨናግፏል-አልተጨናገፈም ለሚለዉ ጥያቄ፥ እኔ እንደማምነዉ እቅዱ ተጨናግፏል ማለት የተጣደፈ ነዉ።ዕቅዱ አሁንም እንዳለ ነዉ።»የዓለም ብቸኛ ሐያሊቱ ሐገር ትልቅ ዲፕሎማት ግን የአንጋፋዉን ዲፕሎማት ትልቅ ምክር ጠንካራ ተስፋ ለመጋራት አልፈቀዱም።እንዲያዉም ለአናን አዛኝ ሆነዉ ለፉ አሏችዉ-የዩናይትድ ስቴትስዋ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሒላሪ ክሊንተን።ሮብ

«ሶሪያ ዉስጥ የሚካሔደዉ ግጭት መቀጠሉ አሳስቦናል።እና ልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማማዋዋልና ግጭቱን ለማስቆም በሚያደርጉት ጥረት የገጠማቸዉ ችግርም አሳስቦናል።»

የተኩስ አቁሙ ዉል ገቢራዊ እንዲሆን በተያዘለት ቀን ግን ወይዘሮ ክሊንተንን ጨምሮ ብዙዎች ሶሪያ ላይ ይሆናል ብለዉ ያልጠበቁት ሆነ።የደማስቆ ተቃዋሚዎች ግምት በግምት፣ የደጋፊ አስታጣቂዎቻቸዉ ትንቢት መና ቀረ።አስራ-ሰወስት ወራት የተንፈቀፈቀዉ አፈሙዝ ላንቃ ባብዛኛዉ ተዘጋ።ሐሙስ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያዉ አምባሳደር በሽር አል-ጅዓፈሪይ እንዳሉት የተኩስ አቁሙ ስምምነት መፅናት፥ የፕሬዝዳት በሽር አል-አሰድ መንግሥት የገባዉን ቃል አያከብርም እያሉ ለሚያወግዙ፣ ለሚወነጅሉት ሐይላት ሐፍረት፣ለስርዓታቸዉና ለደጋፊዎቹ ኩራት ብጤ ነበር።

«ኳሷ አሁን የሶሪያን ታጣቂ ቡድናት በሚደግፉ ወገኖች ሜዳ ዉስጥ ናት።እነዚሕ መንግሥታትና ቡድናት ስምምነቱንና የኮፊ አናን የባለሥድስት ነጥብ ዕቅድ መንፈስን በማክበሩ ሒደት መሳተፍ አለባቸዉ።»

የሶሪያ መንግሥት የኮፊ አናንን ባለሥልድስት ነጥብ የሠላም ዕቅድ መቀበሉን በሚያስታዉቅበት ሰሞን ባለፈዉ ወር ማብቂያ ኢስታንቡል ቱርክ ዉስጥ የተሰበሰቡት የሰባ-አንድ መንግሥታት ተወካዮች ከሰላም እቅዱ ይልቅ የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ነበር የተስማሙት።ከቱርክ እስከ ዋሽንግተን፥ ከስዑዲ አረቢያ-እስከ ፈረንሳይ፥ ከለንደን እስከ ቀጠር የሚገኙ መንግሥታት የተወከሉበት የሶሪያ ወዳጆች የተሰኘዉ ቡድን ስብሰባ ባበቃ በሁለተኛዉ ሳምንት ዩናትድ ስቴትስ ለሶሪያ ተቃዋሚዎች አስራ-ሁለት ሚሊዮን ዶላር ለመለገስ ቃል ገብታለች።

የዋሽንግተን ባለሥልጣናት እንዳሉት ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ያፀደቁት የገንዘብ ርዳታ ለሶሪያ ደፈጣ ተዋጊዎች አልባሳት፥ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ የሌሊት መመልከቻ ባትሪዎች መግዢያ የሚዉል ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስ ፥ ባለሥልጣናቷ እንደሚሉት ለሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች «ገዳይ መሳሪያዎችን» ማስታጠቁን አልፈለገችዉም።

የስዑዲ አረቢያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ልዑል ሳዑድ አል-ፈይሰል ዱባይ ላይ «የሶሪያ አማፂያንን ማስታጠቅ፥ ለተዋጊዎቹ ሙሉ ደሞዝ መክፈል አለብን» እያሉ ሲፎክሩ ግን የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወይዘሮ ክሊኒተን አጠገባቸዉ ነበሩ።ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ክርስቶፍ ሆርስተለር እንደሚሉዉ ደግሞ ባለፈዉ ወር ማብቂያ ዱባይ ላይ የተባለዉም ሆነ ኢስታንቡል የተወሰነዉ ለሩቁ እንጂ፥ «የሶሪያ ነፃ ጦር» ለተሰኘዉ አማፂ ቡድን ተዋጊዎች፥ ሌሎቹ ተቃዋሚዎችም ሆነ ለዓለም ዘዋሪዎች እንግዳ አይደለም።

ምክንያቱም ሆርስትለር እንደፃፈዉ የስዑዲ አረቢያ፥ የቀጠርና የአካባቢዎቻቸዉ ነገስታት የሶሪያ ደፈጣ ተዋጊዎችን ማስታጠቅ፥ ቱርክ ተዋጊዎቹን ማደራጀት፥ መጠለያ መስጠት ከጀመሩ ቆይተዋል።በቅርቡ የትሪፖሊን ቤተ-መንግሥት የተቆጣጠሩት የሊቢያ ገዢዎች እንኳን የወደመች ሐገራቸዉን ከሚጠግኑበት ቀንሰዉ አንድ መቶ ሚሊን ዶላር ለሶሪያ ተቃዋሚዎች ሰጥተዋል።

የአረብና የምዕራብ ሐገራት ለሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች የሚሰጡትን ድጋፍ፥ በተለይም የባሕረ-ሠላጤዉ ነገስታት አማፂያንን በይፋ ለማስታጠቅ መወሰናቸዉን ከአረቦቹ መሐል ኢራቅና ግብፅ ከሐያላኑ ሩሲያና ቻይና ተቃዉመዉታል።የሶሪያ መንግሥት ደጋፊ የምትባለዉ የሩሲያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በዚያዉ ሰሞን እንዳሉት ደግሞ የሶሪያ አማፂያን የዉጪ ሐይላት የሶሪያ ደፈጣ ተዋጊዎችን እስካፍንጫቸዉ ቢያስታጥቁ እንኳን ደም መፋሰሱን ከማባባስ ሌላ፥ ተቃዋሚዎቹ የሶሪያን ጦር ሊያሸንፉ አችሉም።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ በሶሪያዉ የርስ በርስ ጦርነት ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።አንድ ሚሊዮን አንድም ተፈናቅሏል-አለያም ተሰዷል።ሐሙስ የፀናዉ የተኩስ አቁም ተጨማሪ ሕይወት፥ አካል ሐብት ንብረት እንዳይጠፋ ለመከላከል መጠቅሙ አያከራክርም።እራሳቸዉን «የሶሪያ ወዳጆች» የሚሉ ሐይላትም አንዱን ደግፎ ሌላዉን ከማዉገዝ ይልቅ ተፋላሚዎች ለሰላም እንዲገዙ ካግባቡ በርግጥ የሶሪያ-የምድሩ ሳይሆን የሕዝቡ እዉነተኛ ወዳጅነታቸዉን አረጋገጡ ማለት ነዉ።

የዩናይትድ ስቴትሷ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ግን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ገቢር መሆኑ በተረጋገጠበት ዕለት፥ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ታዛቢ ቡድን ለመላክ ሊወስን በተዘጋጀበት ወቅት እንኳን ፕሬዝዳት በሽር አል-አሰድ መወገድ አለባቸዉ እንዳሉ ነበር።

«ሥርዓቱ በገዛ ሕዝቡ ላይ የከፈተዉ ጦርነት እስከመጨረሻዉ ድረስ መቆም አለበት በሚለዉ እምነታችን እንደፀናን ነዉ።አሰድ መወገድ አለባቸዉ።እና የሶሪያ ሕዝብ መፃኤ እድሉን እንዲነድፍ መብት ሊሰጠዉ ይገባል።»

የሶሪያ ሕዝብ ኑሮ አኗኗሩን እራሱ መወሰን አለበት። ደግሞ በተቃራኒዉ የሶሪያ ፕሬዝዳት መወገድ አለባቸዉ። እንደ ቃል-ፍላጎቱ ተቃራኒ መልዕክት ሁሉ በሶሪያዎች ግጭት፥በየተፋላሚ ወገናቱ ደጋፊዎች ሽኩቻ፥ በዋሽንግተኖች ዛቻ-ፉከራ መሐል የፀናዉ ተኩስ አቁም፥ የታዛቢ ቡድኑ ዘመቻ ጥቅል የሠላም እቅዱን ገቢር ለማድረግ መተከራቸዉ ነዉ የቀቢፀ ተስፋዉ ድምቀት።ግን ሶሪያ መካከለኛዉ ምሥራቅ ናት።የተስፋ-ቀቢፀ ተስፋ ጥምር እዉነት ምድር።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ሲሆን ያሰማን።

U.N.-Arab League envoy Kofi Annan (R) meets with Turkey's Deputy Prime Minister Besir Atalay at Hatay airport, southern Turkey, April 10, 2012. Annan said there should be no preconditions to halting violence in Syria and insisted a U.N.-sponsored peace plan designed to stem 13-months of conflict was still on the table. Speaking just hours before the end-of-day deadline for Syria to implement the ceasefire plan, Annan said Syrian forces had withdrawn from some areas but moved to others not previously targeted, and the situation was not as he had hoped. REUTERS/Bulent Kilic/Pool (TURKEY - Tags: POLITICS CIVIL UNREST SOCIETY IMMIGRATION)
አናንምስል Reuters
epa03183525 An undated handout photograph made available by the Local Coordination Committes (LCC) in Syria on 15 April 2012, shows people demonstrating in Kafar Nobbol, near Idlib, Syria. According to media reports on 15 April, A first group of an advance team of UN monitors was en route to Damascus and was set to arrive on 15 April at night, the spokesman of international envoy Kofi Annan said. Starting on 16 April, the six-person group 'will deploy to centers where there has been conflict,' after consulting with Syrian authorities. The rest of the advance team, which is to number 25 to 30 people, would follow 'as soon as possible'. EPA/LOCAL COORDINATION COMMITTES LCC BEST QUALITY AVAILABLE. EPA IS USING AN IMAGE FORM AN ALTERNATIVE SOURCE, THEREFORE EPA CAN NOT CONFIRM THE EXACT DATE AND SOURCE OF THE IMAGE HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES
ሰላምና ጦርነትምስል picture-alliance/dpa

ነጋሽ መሐመድ

እርያም ተክሌ

















ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ