1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማልያ እና የሰብዓዊው ርዳታ አቅርቦት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 16 1999

በሶማልያ የቀጠለውን ውዝግብና በመዲናይቱ የሚካሄደውን ውጊያ ሸሽቶ የተፈናቀለውን ሕዝብ ለመርዳት በሀገሪቱ የተሰማሩት የርዳታ ድርጅቶች ከሽግግሩ መንግሥት አኳያ ገደብ እንዳረፈባቸው ያሰሙትን ወቀሳ የሽግግሩ መንግሥት ባስቸኳይ እንዲያያነሳ በኬንያ የሚገኙት የዩኤስ አሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራነንበርገር ለፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍ በጻፉት ደብዳቤ አሳሰቡ። የርዳታ ድርጅቶቹ ገጠማቸው ስለተባለው ችግር አርያም ተክሌ የሶማልያ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤ

https://p.dw.com/p/E0YT
ተፈናቃይ ሶማልያውያን
ተፈናቃይ ሶማልያውያንምስል AP

�� ባለሥልጣን አብዱራዛክ ሀሰን አደምን በስልክ አነጋግራቸዋለች።

ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ እየከፋ የሄደው የሰብዓዊ ሁኔታ እንዳሳሰባት አስታወቀች። የዩኤስ አሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራነንበርገር፡ በተለይ በመዲናይቱ ሞቃዲሾ የቀጠለውን ውጊያ ሸሽቶ በመዲናይቱ አቅራቢያና በጁባ አካባቢ ለሚገኘው ተፈናቃይ የሰብዓዊ ርዳታ የሚያቀርቡት ድርጅቶች ገጠመን ያሉትን ችግር የሽግግሩ መንግሥት ባስቸኳይ ርምጃ ወስዶ እንዲያስወግድ ጠይቀዋል። በሶማልያ የተሰማሩት የርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ርዳታ በሚያጓጉዙበት ሥራቸው በሀገሪቱ አየር ማረፊያ እንዳይጠቀሙ ወይም የሽግግሩን መንግሥት ፈቃድ ሳያገኙ በፊት ርዳታ እንዳያከፋፍሉ የመሳሰለውን ዓይነት ገደብ ማሳረፉን የተመድ የሰብዓዊ ርዳታ አስተባባሪ ድርጅት ያቀረበውን ወቀሳ አምባሳደሩ በማስረጃነት አቅርበዋል። እርግጥ፡ በመሠረቱ የሶማልያ የሽግግር መንግሥት በመላ ሶማልያ የርዳታ አቅርቦቱ ተግባር ለማቃለል የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ የሶማልያ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብዱራዛክ ሀሰን አደም አስታውቀዋል። ይሁንና፡ ድርጅቶቹ በሥራቸው ክንውን ላይ ከሽግግሩ መንግሥት አኳያ ገጠመን በሚል ካለፈው ሣምንት ወዲህ አጉልተው ያቀረቡት ችግር በሀገሪቱ ካለፉት አሥራ ስድስት ዓመታት ወዲህ ያለ መሆኑን ነው አብዱራዛክ ሀሰን አደም ያመለከቱት።
« ዓለም አቀፉ ማሕበረ ሰብ ባጠቃላይ በወቅቱ ያሰማው ቅሬታ በሀገሪቱ ከብዙ ዓመታት ወዲህ የሚታየውን ችግር የሚያንፀባርቅ ነው። መንገዶቹ ጥሩ አይደሉም፤ የአየር ማረፊያዎቹም አይመቹም። የፀጥታ ችግሮችም አሉ። እና የሰብዓዊውን ርዳታ ለማከፋፈል የሚሞክሩት በዚህ በዓቢይ ጦርነት መሀል መሆኑ ነው። »
ባለሥልጣኑ አክለው እንዳስረዱት፡ የሽግግሩ መንግሥት ከርዳታ ድርጅቶች ጋር ባደረጋቸው የተለያዩ ውይይቶች ላይ የቀረቡለትን ጥያቄዎች በጠቅላላ ለማሟላት ሞክሮዋል። ድርጅቶቹ አሉ የሚሉዋቸውን ችግሮች በግልፅ እስካስቀመጡ ድረስ የሶማልያ የሽግግር መንግሥት እሮዋቸው ተባብሮ ለመሥራት ችግር እንደሌለበት አብዱራዛክ አስታውቀዋል።
« በሶማልያ የሚታዩትን አጠቃላይ መዋቅራዊ ችግሮች የሀገሪቱ መንግሥት ሆን ብሎ የፈጠራቸው አስመስሎ ለማቅረብ ነው የተፈለገው። ይሁንና፡ ለችግሩ ተጠያቂው መንግሥት መሆኑን ማረጋገጥ ከቻሉ፡ መንግሥት የርዳታ አቅርቦቱን የማከፋፈሉን ሥራ ለማመቻቸት ዝግጁ ነው። »
እንደሚመስለኝ፡ በሶማልያ ያሉትን ችግረኞች በመርዳቱ ተግባራቸው ላይ ምን ያህል ውጤታማ መሆናቸውን በተመለከተ ሊነሳባቸው የሚችለውን ነቀፌታ ከራሳቸው ለማራቅ በመሞከር ላይ ናቸው። እና ይህንን ወቀሳ ለማራቅም ሲሉ በወቅቱ የሶማልያ መንግሥት አይረዳንም፤ ወይም መንግሥቱ በአንፃራችን እንቅፋት ደቅነዋል የሚል ምክንያት ለማቅረብ ነው የሚሞክሩት። »