1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ጥር 28 2010

በ ሴቶች 1500 ሜትር የሩጫ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛውን የአለም ፈጣን ሰአት በማስመዝገብ አሸናፊ በመሆን 10 ነጥብ አግኝታለች ።ገንዘቤ የገባችበት ሰአት 3፥ 55፥45 በአለም ከተመዘገበው ፈጣን ሰአት 5 ኛው ነው።

https://p.dw.com/p/2sAP3
Fußball Bundesliga | 20. Spieltag | Leverkusen - Mainz
ምስል Reuters/W. Rattay

የጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም. የስፖርት መሰናዶ

በአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽ ማህበር የበላይ አስተባባሪነት የሚዘጋጀው  6 ተከታታይ የቤት ወስጥ ውድድር ቅዳሜ ለት በካርልስሩህ  ጀርመን ሲጀመር

ኢትዮጵያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በሁለት የውድድር አይነት ተካፋይ ሆነዋል። በ ሴቶች 1500 ሚትር ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛውን የአለም ፈጣን ሰአት በማስመዝገብ አሸናፊ በመሆን 10 ነጥብ አግኝታለች  ገንዘቤ የገባችበት ሰአት 3፥ 55፥45   በአለም ከተመዘገበው ፈጣን ሰአት 5 ኛው ነው ። ጀርመናዊትዋ አትሌት ኮንስታንዝ/ስ ክሎስተርሀይፈን  ሁለተኛ በመወጣት 7 ነጥብ ስታገኝ  ኬንያዊትዋ ብትሪስ ኪፕ ኮች  ሶስተኛ በመሆን 5 ነጥብ አግኝታለች ። በወንዶች 3000 ሼህ ሚትር ሀጎስ ገብረህይወት 7.37.91 ሰከንድ ቀዳሚሲሆን ዮሚፍ ቀጀልቻ የራሱን ሰአት በማሻሻል 7፥38፥67 ሁለተኛ በመሆን 7 ነጥብ ሲያገኝኛ ሶስትኛው የሞሮኮው አትሌት አብደላቲ ኢጉዲር ወጥቷል። የዓለም የቢት ውስጥ ተከታታይ ውድድር ነገ በ ጀርመን ሀሙስ በስፒን የፊታችን ቅዳሚ በአሜሪካ ይካሂድ እና እንደገና ወደ አውሮፓ ከተሞች ተማልሲ በፖላንድ እና በስኮትላንድ በመካዮድ ከ ሁለት ሳምንት በሁዋላ ይጠናቀቃል።

የአለማቀፍ አትሌቲክስ ማህበር የፀረጉልብት ሰጭ መድኃኒት ተቆጣጣሪ ቦርድ  18 ራሺያ አትሌቶች ነፃ በመሆን እንዲወዳደሩ ፈቅድዋል፤ ከሰማኒያ በላይ የራሺያ አትሌቶችን ማመልከቻ ተቀበሎ የተመለከተ መሆኑን  የገለፀው  ተቆጣጣሪ ቦርድ  በመጭው ወር በሚደረገው የበርሚንግሃም  የአለም የቢት ውስጥ ወድድር ላይ ለሚካፈሉ አትሌቶች ቅድሚያ መስጠቱን  አስታውቋል።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ