1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞች ከመስመጥ ዳኑ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2008

የስደተኞቹን ሕይወት በማዳኑ ጥረት ከባሕር ሐይሉ ባልደረቦች በተጨማሪ የበጎ ፍቃደኛ ነብስ አድን ሰራተኞችም ተሳትፈዉ ነበር።አንዲት የኖርዌ መርከብም ከሰባት መቶ በላይ ስደተኞች ከመስመጥ አድናለች።

https://p.dw.com/p/1JsKM
ምስል picture alliance/AP Photo/E. Morenatti

[No title]

የኢጣሊያ ባሕር ኃይል ሜድትራኒያን ባሕር ላይ ሲቀዝፉ ለአደጋ የተጋለጡ ከ6ሺሕ አምስት መቶ በላይ ስደተኞች ትናንት ማዳኑን አስታወቀ።የባሕር ሐይሉ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በአራት አነስተኛ ጀልባዎች ተሳፍረዉ ይጓዙ የነበሩት ስደተኞች ቁጥር ጀልባዎቹ ከሚሸከሙት በላይ ሥለነበር ጀልባዎቹ ለመስመጥ ተቃርበዉ ነበር።የስደተኞቹን ሕይወት በማዳኑ ጥረት ከባሕር ሐይሉ ባልደረቦች በተጨማሪ የበጎ ፍቃደኛ ነብስ አድን ሰራተኞችም ተሳትፈዉ ነበር።አንዲት የኖርዌ መርከብም ከሰባት መቶ በላይ ስደተኞች ከመስመጥ አድናለች።ሥለስደተኞቹ ጉዞና ከመስመጥ ሥለማዳኑ ጥረት የሮም ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ተኽለእግዚ ገብረየሱስን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ