ስዊድን ዉስጥ የኤርትራ መሪዎች ላይ ክስ መመሥረቱ፤
ሐሙስ፣ ሰኔ 26 2006ማስታወቂያ
የክስ ማመልከቻዉን ለፖሊስ ያቀረቡት ፔርሲ ብራት፣ የሱ ሳልካ እና የፓሪሱ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሕግ ባለሙያ ፕሪስካ ኦርሶኖ ሲሆኑ፣ ክስ ያቀረቡት በኤርትራ ፕሬዝደንት እና ሚኒስትሮቻቸዉ ላይ ነዉ። ክሱ የቀረበዉ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የሕግ፣ የመከላከያና የዉጭ ሚኒስትሮችና በፕሬዝደንቱ ልዩ አማካሪ ላይ መሆኑን የስቶክሆልም ወኪላችን ቴድሮስ ምህረቱ በላከዉ ዘገባ ገልጿል።
ቴድሮስ ምህረቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ