1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስዊድንና አዲሱ የድንበር ቁጥጥር

ማክሰኞ፣ ጥር 3 2008

በጎርጎሮሳውያኑ 2015 ዓም በርካታ ተገን ጠያቂዎችን ያስገባችው ስዊድን የድንበር ቁጥጥር ከጀመረችበት ካለፈው ሳምንት ሰኞ አንስቶ ወደ ሃገርዋ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መቀነሱን አስታውቃለች።

https://p.dw.com/p/1Hc64
Dänisch-Schwedischer Grenzübergang Kontrolle
ምስል picture-alliance/dpa/A. Ladefoged

9.8 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ስዊድን በጎርጎሮሳዊው 2015163 ሺህ ተገን ጠያቂዎችን ነበር ወደ ሃገርዋ ያስገባችው ። ባለሥልጣናት እንደሚሉት ከዚህ ቀደም ሰዎች በነፃ በሚዘዋወሩበት ድንበር ላይ የጉዞ ሰነድ ቁጥጥር ተግባራዊ በተደረገበት በመጀመሪያው ሳምንት ሃገሪቱ 1500 የተገን ጥያቄ ማመልከቻዎችን ነው የተቀበለችው ። ባለፈው ጥቅምትና ህዳር ወር ውስጥ ግን ስዊድን በየሳምንቱ የምትቀበለው ወደ 10 ሺህ የሚጠጋ የተገን ጠያቂዎችን ማመልከቻ ነበር ። ስዊድን የድንበር ቁጥጥር ተግባራዊ ካደረገች ከአንድ ሳምንት በኋላ ሁኔታዎች ምን ይመስላሉ። ስዊድንና አዲሱ የድንበር ቁጥጥር በተመለከተ የስቶክሆልሙን ወኪላችንን አነጋግረነዋል።

ቴድሮስ ምህረቱን

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ