1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለHIV/AIDS ግንዛቤን ለማስፋት የበጎ ፈቃደኞች ጥረት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 2 2008

በሶስት ሰዎች ተነሳሽነት ሰብዓዊነት የተላበሰዉ ሥራ የተጀመረዉ የዛሬ 12ዓመት ነበር። ወደአገር ቤት በሄዱበት አጋጣሚ HIV/ADIS ወላጆቻቸዉን የቀማቸዉ ልጆች ያሉበትን አስከፊ የኑሮ ሁኔታ መመልከታቸዉ ለዚህ እንዳነሳሳቸዉ ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/1GnR0
Gemeinsamer Arm Gegen Aids e.V. Preisverleihung
ምስል Gemeinsamer Arm Gegen Aids e.V.

ግንዛቤን ለማስፋት የበጎ ፈቃደኞች ጥረት

እርግጥ ነዉ ሀገር፤ ሀገር ነዉ እና ለወገኖቻቸዉ ከዚህ የአቅማቸዉን ለማድረግ ቃል ተገባቡ። በዚህም አላበቃ፤ ወደጀርመን ተሰደዉ በየስደተኛ ማቆያ ጣቢያ የሚገኙ እና ተመሳሳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸዉ መኖራቸዉን መረዳታቸዉ ዕቅዳቸዉን አሰፋዉ። ግን አልተበገሩም ሶስት ሆነዉ ብዙዎች ካልተስማሙ በቀር ሊያከናዉኑት የማይችሉትን አርአያነት ያለዉ ሥራ ሠርተዉ ዘንድሮ ለሽልማት በቁ። በሶስት በጎ ፈቃደኞች የሚንቀሳቀሰዉ የሕብረት ክንድ በኤድስ ላይ ማኅበር ወይም በጀርመንኛዉ Gemeinsamer Arm Gegen Aids e.v. ያለምንም የገንዘብ ድጋፍ በሰብዓዊነት ላበረከተዉ ትርጉም ያለዉ አገልግሎት ባለፈዉ ግንቦት ወር ነበርበፌደራልጀርመንየጤናጥበቃሚኒስቴርየተሸለመዉ።

Gemeinsamer Arm Gegen Aids e.V. Preisverleihung
ምስል Gemeinsamer Arm Gegen Aids e.V.

ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2008ዓ,ም ማኅበሩየተመሠረተበትን 12ኛ ዓመት እና እዚህ ጀርመን ሃገር ከሚንቀሳቀሱ 100 ፕሮጀክቶች ጋር ተወዳድሮ የተሸለመበትን ደስታ ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ኑረንበርግ ከተማ ላይ አክብሯል።

በዝግጅቱ ላይ የኑረንበርግ ከንቲባ ወኪል ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ለHIV/AIDS የምክር አገልግሎት የሚሰጠዉ የጀርመን ማዕከል የኑረንበር ኃላፊ ካተሪን ሽትሮሆፈርም በሽታዉ በጀርመን ያለበትን ሁኔታ አብራርተዋል። በተደረገዉ ገለፃ መሠረትም ስደተኛ ማቆያ ጣቢያ ስገቡ ምርመራ ተደርጎላቸዉ HIV በደማቸዉ ዉስጥ የሚገኝ ቁጥራቸዉ ቀላል አይባልም። ከእነሱ መካከል ደግሞ የኢትዮጵያዉያኑ ቁጥር ሚዛን የሚደፋ መሆኑን በቀረበዉ አንድ ማሳያ መረዳት ይቻላል። ይኸዉም በቅርቡ ምርመራ ተደርጎላቸዉ HIV ተሐዋሲ በደማቸዉ ከተገኘ 38 ሰዎች መካከል 13ቱ ኢትዮጵያዉያን መሆናቸዉ ተገልጿል። እንዲህ ያለዉ ማኅበር በመኖሩም የማኅበሩ ሶስት አባላት በየጊዜዉ ወደስደተኛ ማቆያ ስፍራ ምግብ አዘጋጅተዉ በመሄድ ቡና ተፈልቶ ከጥገኝነት ፈላጊዎቹ ጋር በሚኖራቸዉ ቆይታ ስለምርመራዉ አስፈላጊነት፤ ስለበሽታዉ መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ ስልቶች ይነጋገራሉ። HIV በደማቸዉ እንደሚገኝ ያወቁትን ደግሞ መድኃኒት የሚያገኙበትን መንገድ መምራት እና ማበረታታቱ ትልቁ ተግባራቸዉ ነዉ።

Gemeinsamer Arm Gegen Aids e.V. Preisverleihung
ምስል Gemeinsamer Arm Gegen Aids e.V.

የሕብረት ክንድ በኤድስ ላይ ማኅበር ሃሳብ ጠንሳሽና ላለፉት 12ዓመታትም ጊዜያቸዉን በበጎ ፈቃደኝነት ለዚህ ተግባር ያዋሉትን የዘንድሮዉን የፌደራል ጀርመን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተሸላሚዎች ከቅዳሜዉ ዝግጅታቸዉ በኋላ አረፍ ብለዉ ስላከናወኑት ተግባር ተወያየን።

ዝግጅቱን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ