1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከእስር የተፈቱ ኢትዮጵያውያን ሐገራቸው ተመለሱ

ሰኞ፣ ግንቦት 13 2010

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 1085 ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን  ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/2y4Ni
Boeing 787 Ethiopian Airlines
ምስል Reuters

ሳዑዲ የፈታታቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች ሀገራቸው ገቡ

ሳዑዲ አረብያ በምሕረት ከእስር የለቀቀቻቸው ኢትዮጵያውያን እሥረኞች ከትናንት በስተያ አንስቶ ወደ ሀገራቸው ገብተዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 1085 ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን  ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። እስረኞቹ የተፈቱት በቅርቡ ሳውዲ አረብያን የጎበኙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያውያኑ እንዲፈቱ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መሆኑን መንግሥት አስታውቋል። ከሳዑዲ እስር ቤቶች ስለተፈቱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የጅዳውን ወኪላችንን ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነብዩ ሲራክ 
ኂሩት መለሰ