1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ሳዑዲ አረቢያ የሙስና ተጠርጣሪዎችን ለቀቀች

ማክሰኞ፣ ጥር 22 2010

ኢትዮጵያዊዉ ሳዑዲ አረቢያዊዉ ቱጃር ሼኽ መሐመድ ሁሴይን አል አሙዲ ግን ሥለመለቀቅ አለመለቀቃቸዉ ምንም የታወቀ ነገር የለም።

https://p.dw.com/p/2rmRZ
Ritz-Carlton in Saudi Arabien
ምስል picture-alliance/augenklick/firo Sportphoto/El-Saqqa

(Q&A) Saudi Arabia Released Detainees - MP3-Stereo

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ባለፈዉ ሕዳር በሙስና ጠርጥሮ ያሰራቸዉን አብዛኞቹን ልዑላን፤ የቀድሞ ባለሥልጣናት እና ቱጃሮችን ለቀቀ።የሐገሪቱ ማስታወቂያ ሚንስቴር ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ተጠርጣሪዎቹ በሙሉ ከነበሩበት ሆቴል  ወጥተቃል።በመግለጫዉ መሠረት ከታሰሩት መከካል 381ዱ ሲለቀቁ፤ የተቀሩት 56ት እስረኞች ወደሌላ እስር ቤት ተዛዉረዋል።መንግሥት ከተለቀቁት እስረኞች ከ106 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማስመለሱ ተዘግቧልም።ኢትዮጵያዊዉ ሳዑዲ አረቢያዊዉ ቱጃር ሼኽ መሐመድ ሁሴይን አል አሙዲ ግን ሥለመለቀቅ አለመለቀቃቸዉ ምንም የታወቀ ነገር የለም።

ስለሺ ሽብሩ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ