1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳን ውስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማሳሰቢያ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 4 2011

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በሱዳን የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚኖሩ የገለጠው ኤምባሲው ኢትዮጵያውያኑ ሱዳናውያን ሰልፍ ከሚያካሂዱባቸው ሥፍራዎች ራሳቸውን እንዲያርቊ መክሯል። ኢትዮጵያውያኑ ችግር ካጋጠማቸዉ የኤምባሲው ሠራተኞችን እንዲያነጋግሩ ስድስት የተለያዩ ስልክ ቁጥሮችን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች አሰራጭቷል።

https://p.dw.com/p/3GgnU
Demonstration Sudan Karthoum
ምስል Reuters

ሱዳን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳሰበ

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በሱዳን የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚኖሩ የገለጠው ኤምባሲው ኢትዮጵያውያኑ ሱዳናውያን ሰልፍ ከሚያካሂዱባቸው ሥፍራዎች ራሳቸውን እንዲያርቊ መክሯል። ኢትዮጵያውያኑ ችግር ካጋጠማቸዉ የኤምባሲው ሠራተኞችን እንዲያነጋግሩ ስድስት የተለያዩ ስልክ ቁጥሮችን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች አሰራጭቷል።  

በሱዳን ኤምባሲ የዲያስፖራ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ አቶ ነጂብ አብደላ ኢትዮጵያውያኑ፦ «ሱዳን ውስጥ አኹን ካለው ኹኔታ አንፃር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ» መክረዋል። የአኹኑ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፦ «ማታ በሱዳን ሰዓት አቆጣጠር ከአራት ሰአት፤ እስከ ንጋቱ ዐሥር ሰአት ድረስ የሰአት እላፊ ወይንም ደግሞ መንቀሳቀስ የሚገድብ ነው» ሲሉ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። የሰዓት እላፊዉ ገደብ ላንድ ወር  የሚፀና ነዉ።አዲሱ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ለ3 ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓልም።

አቶ ነጂብ፦ «አንዳንድ ኢትዮጵያውያን በወጣትነት ስሜት በየአካባቢው የሚደረገው እንቅስቃሴ ደስ ስለሚላቸው ዝም ብለው ሄደው ጎብኝተን መጣን ይላሉ» ይሕን መሰሉ ድርጊት  «አደገኛ» መሆኑን ጠቊመዋል። በመዲናዪቱ ካርቱም ቤተመንግሥት አካባቢ፤ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በብዛት የሚገኙባቸው «የሱዳን ክፍለ-ሃገራት፦ ገዳሪፍ፣ ከሠላ፤ ፖርት ሱዳን፣ ሰባኪን፣  መዳኒ፣  አድ ደማዚን፣ ሲናር፣ ሲንጃ እንዲሁም ምሥራቃዊ ሱዳን በብዛት ኢትዮጵያውያን ስለሚገኙ» አመጽ በሚካሄድባቸው ሥፍራዎች እንዳይገኙ ኤምባሲው አሳስቧል።  ሱዳን ነዋሪ የኾኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ችግር ቢገጥማቸው ለኤምባሲው ሪፖርት እንዲያደርጉ የተዘጋጁት ስልክ ቊጥሮች ከእነ ሱዳን ኮዳቸው የሚከተሉት ናቸው።

00249-911646547፣

00249-922697642፣

00249-900410075፣

00249-121111465፣

00249-912534834፣  

00249-900368617፣

በሥራ ሰአት የኤምባሲው ጽ/ቤት ስልክ የሚከተለው ነው፦ 00249-183471156።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ