ሰላም የራቃት የመን
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 14 2008ማስታወቂያ
በኢራን እንደሚደገፍ የሚነገርለት ሁቲ አማፅያን መሪ ግን ከወዲሁ የመንግሥታቱ ድርጅት ያሰናዳዉ ድርድር ትርጉም የለዉም በማለት ደጋፊዎቻቸዉ የመንግሥት ደጋፊ ኃይሎች ዋና ከተማ ሰንዓን እንዳይዙ እንዲከላከሉ ተማፅነዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በአማፅያኑ እና በመንግሥት ኃይሎች የተጣሰዉ የተኩስ አቁም ፀንቶ እንዲከበር እየጠየቀ ነዉ። ሁቲ አማፅያኑ የተኩስ አቁሙ ታዉጆ የመንግሥት ኃይሎች ጥቃት አድርሰዉብናል እያሉ ነዉ። የሰላም ዉይይቱን መቃወም የጀመሩት በዚህ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነዉ የተገለጸዉ። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ ሰንዓ የሚገኘዉን ጋዜጠኛ ግሩም ተክለ ኃይማኖትን ስለሁኔታዉ አነጋግሬዋለሁ።
ግሩም ተክለ ኃይማኖት
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ