1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሮቤል ተመስገን

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2004

«መኪና ግዙልኝ» ፕሮጀክት እና ስራዎቹ«ኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ ያላቸው ሼክ አላሙዲም ቢሆኑ አንድ ብር ነው እንዲሰጡኝ የምፈልገው። በዝቅተኛ ደረጃ የሚኖር አንድ ሰውም ፍቃደኛ ሆኖ ከሰጠኝ አንድ ብር ብቻ ነው የምቀበለው።»

https://p.dw.com/p/14cPV
Titel:Robel Temesgen Schlagworte: Äthiopien, Künstler Wer hat das Bild gemacht?: Das Bild wurde durch der Künstler selbst für die Nutzung zur Verfügung gestellt. Wann wurde das Bild gemacht?: 2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: In Deutschland Bildbeschreibung: Robel Temesgen bei einer Kunstaustellung in Deutschland Bildrechte: Das Bild wurde durch der Künstler selbst für die Nutzung der DW zur Verfügung gestellt.
ሮቤል ተመስገንምስል Robel Temesgen

በሳምንቱ መጀመሪያ የዓለምእጅግ የተከበሩ ሎሬትሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። «የዓለምእጅግ የተከበረ ሎሬት» የሚል ማዕረግ የተሰጣቸዉን አፈወርቅ ተክሌ በስዕል ጥበብ እዉቀተቻዉና በምርጥ ስዕሎቻቸዉ ከኢትዮጵያ አልፈዉ በዓለም የሥነ-ጥበብ መድረክ የመጨረሻ ጫፍ የደረሱ ክቡር የጥበብ ሰዉ ነበሩ። ወጣት ሰዓሊያን ከሳቸው ምን መማር ችለዋል? አድናቂያቸው ወጣት ሰዓሊ ሮቤል ተመስገን አርዓያዬ ከሚላቸው ዝነኛ ሰዓሊ ስለተማረው እና ስለ ራሱ ስራዎች ያጫውተናል።

ሮቤል ወደ ጀርመን በርሊን ብቅ ብሎም በአንድ «ሰርቫይቭአርት» የስዕል አውደ ርዕይ ላይ ተካፍሏል። ከሌሎች ኢትዮጵያን ሰዓሊዎች ጋ ተወዳድሮ ወደ ጀርመን ከመጡት ሁለት ኢትዮጵያውያን ሰዓሊያን አንዱ ነው። ያተኮረበትም ርዕስ «ሴት እና ወንድ» ይሰኛል። በቪዲዮ መልክ የቀረበ ስነ ጥበብ ነው። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ሮቤል ጋቢ ለብሶ የተነሳውን ፎቶ የተመለከትን አንጠፋም። ይህንንም ሆን ብዬ ነው ያደረኩት ይላል። ሚስጥሩን አካፍሎናል። ሁሉንም ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ