ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ የገጠማቸው ተቃውሞ28 ጥር 2001ሐሙስ፣ ጥር 28 2001የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ በ 2 ተኛው የዓለም ጦርነት ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች አልተጨፈጨፉም ፣ በወቅቱም ሰዎችን በመርዘኛ ጋዝ አፍኖ መግደያ ስፍራዎች አልነበሩም ሲሉ ለካዱት ጳጳስ ሪቻርድ ዊልያምሰን በቅርቡ ምህረት በማድረጋቸው ከየአቅጣጫው ተቃውሞ ተነስቶባቸዋል ።https://p.dw.com/p/Go0xቤኔዲክት አስራ ስድስተኛምስል picture-alliance/ dpaማስታወቂያበዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ካቶሊኮች መሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት አስራ ስድሰተኛ ውዝግብ ተለይቷቸው አያውቅም ። ጳጳሱ በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚሰጧቸው አስተያየቶች ሙስሊሞችን ሴቶችን ፖላንዶችን ግብረ ሰዶማውያንና ሳንቲስቶችን አስቆጥተዋል ።