1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

ሦስቱ ተሸላሚ ኢትዮጵያውያን

ረቡዕ፣ መስከረም 28 2012

በቻይና በተደረገው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ሦስት ኢትዮጵያውያን ከዓለም 17ተኛ ከአፍሪካ አልጄሪያን ተከትለው 2ተኛ በመውጣት አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል። ህዋዌ በተባለ የቴክኖሎጂ ድርጅት በተዘጋጀው ይህ ውድድር ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡት ሥራ ከኔትዎርኪንግ ቴክኖሎጂ ጋር የተዛመደ ነው።

https://p.dw.com/p/3QzcM
China, Dongguan: Betriebssystem Huawei Harmony
ምስል picture-alliance/A. Chang

በቻይና ለሽልማት የበቁት ሦስቱ ኢትዮጵያውያን

ሦስት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ቻይና ውስጥ በተደረገ የቴክኖሎጂ ውድድር አሸናፊ ኾነዋል። የመቀሌው ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ያነጋገራቸው እነዚህ የኤምአይቲ ምሩቃን በቀጣይነት በሀገራቸዉ የኔትወርክ ደሕንነት ላይ የመሥራት እቅድ እንዳላቸው ገልፀዋል። ያሬድ ወልደገብርኤል፣ ይብራህ መሓሪና ኤልያስ ኪዳነማርያም የተባሉት እነዚህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሞያዎች ባለፈው ዓመት ነበር ከመቐለ ኢንስቲትዩት ኦፎ ቴክኖሎጂ በኮምፒውተር ሳይንስና ኢንጅነሪንግ የተመረቁት። ከዩኒቨርሲቲያቸው ጀምሮ በየደረጃው እስከ ሀገር በተካሄዱ ውድድሮች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ነበር ለዓለማቀፉ የህዋዌ ቴክኖሎጂ ውድድር የበቁት።

በኔትዎርኪንግ ከኤስያ፣ አውሮፓና አፍሪካ ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በቻይና ሀገር በተደረገ ዓመታዊ ውድድር የተሳተፉት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከዓለም 17 ከአፍቃ ደግሞ ሁለተኛ ሆነው ውድድራቸው አጠናቀዋል፡፡ በቆይታቸው ከውድድር ባለፈ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከመጡ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጠቃሚ ልምድ እንዳገኙም ይገልፃሉ፡፡ ለዛሬው የሳይንስ እና ቴክኒዎሎጂ ያጠናቀረውን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ልኮልናል። ሙሉውን ከድምጽ ዘገባው ያድምጡ።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ