ሥጋት የተደቀነበት የአፍሪቃ ተፈጥሮ አካባቢ
ሐሙስ፣ የካቲት 22 1999በተፈጥሮ አካባቢ --------->
ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከሞላ ጎደል ሁሉንም የአፍሪቃ ሀገሮች በጠቅላላ የሚመለከት ችግር መሆኑን ለተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ የሟገቱት ኬንያዊትዋ ዋንጋሪ ማታይ አስታወቁ። ይህም ቢሆን ግን፡ ችግሩ በአህጉሩ ያን ያህል ትኩረት እንዳላገኘ የኖቤል ሰላም ተሸላሚ ማታይ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪቃ የፀጥታና የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ጉባዔ ላይ ገልፀዋል።