1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ 100 በላይ የሩስያ ዲፕሎማቶችን ተባረሩ  

ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2010

በብሪታንያ የሳልስበሪ ከተማ የሚኖሩ አንድ የቀድሞ የሩሲያ እና የብሪታንያ ድርብ ሰላይ እና ልጃቸዉን ለመግደል የመርዝ ጋዝ ጥቃት ተፈጽሟል ከተባለ በኋላ 16 የአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራት ቢበዛ አራት ቢያንስ አራት የሩስያ ዲፕሎማቶችን ማባረራቸዉን አስታዉቀዋል።  

https://p.dw.com/p/2v5em
Russische Flagge hinter Stacheldraht
ምስል Reuters/G. Garanich

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩልዋ 60 የሩስያ ዲፕሎማቶችን አባራለች

አውሮጳውያቱ ሀገራት በዚሁ የተቀናጀ ርምጃቸው ለመርዝ ጋዙ ጥቃት ተጠያቂ ናት በሚሏት በሩስያ ላይ ግፊታቸውን ለማጠናከር አስበዋል።  ዩናይትድ ስቴትስ በበኩልዋ ስድሳ የሩስያ ዲፕሎማቶችን ማባረርዋን አስታዉቃለች።  ምዕራባዉያኑ ሀገራት የሩስያን ዲፕሎማቶችን ከሃገራቸዉ ለአባረሩበት ርምጃ ሩስያ በሚቀጥሉት ቀናት ተመሳሳይ ምላሽ እንደምትሰጥ ማስታወቅዋይታወቃል። ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባዉን ከብረስልስ ልኮልናል።  

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩልዋ 60 የሩስያ ዲፕሎማቶችን አባራለች