1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለአራተኛ የስልጣን ዘመን ይወዳደራሉ

ሰኞ፣ ኅዳር 12 2009

የጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለአራተኛ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ተናገሩ። አንጌላ ሜርክል ለወግ አጥባቂው ክርስቲያ ዴሞክራቶች ፓርቲ አባላት በሚቀጥለው ዓመት በሚካሔደው ምርጫ ለመወዳደር እንደሚፈልጉም ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/2SzVW
Angela Merkel kandidiert erneut
ምስል Getty Images/S. Gallup

 

 

ባለፉት ወራት መራሂተ መንግሥትዋ እንደሚወዳደሩ መናገራቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮችን ጠቅሶ ሲኤን ኤን የዜና አገልግሎት በሰፊዉ ዘግቦ ነበር።  ሜርክል በሚቀጥለው ወር በሚካሔደው የወግ አጥባቂው ክርስቲያን ዴሞክራቶች ፓርቲ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የ62 አመቷ አንጌላ ሜርክል ራሳቸውን በእጩነት እንደሚያቀርቡም ታዉቋል። የፊዚክስ ባለሙያዋ አንጌላ ሜርክል ወደ መራሒተ መንግሥትነት የመጡት በጎርጎሮሳዊው 2005 ዓ.ም. ሲሆን የመጀመሪያዋ የጀርመን ሴት መሪ ናቸው።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ