1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርት

ማካካሻ ትምሕርት ለተፈናቃዮች

ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2011

ከቤት ንብረታቸዉ በመፈናቀላቸዉ ትምሕርት ላቆረጡ 300,000 የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ዘንድሮ ክረምት የማካካሻ ትምሕርት እንደሚሰጥ  ትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ።የሚንስቴሩ ባለስልጣናት እንደሚሉት ተፈናቃይ ተማሪዎችን ለማስተማር 6000 መደበኛ አስተማሪዎችና 6000 በጎ ፈቃደኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአካባቢዉ ይዘምታሉ።

https://p.dw.com/p/3JwvL
Äthiopien IDPS Benishangul Gumuz
ምስል DW/A. Mekonnen

ለተፈናቃዮች ማካካሻ ትምሕርት ሊሰጥ ነዉ

በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ግጭትና ጥቃትን ሸሽተዉ ከቤት ንብረታቸዉ በመፈናቀላቸዉ ትምሕርት ላቆረጡ 300,000 የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ዘንድሮ ክረምት የማካካሻ ትምሕርት እንደሚሰጥ  ትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ።የሚንስቴሩ ባለስልጣናት እንደሚሉት ተፈናቃይ ተማሪዎችን ለማስተማር 6000 መደበኛ አስተማሪዎችና 6000 በጎ ፈቃደኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአካባቢዉ ይዘምታሉ።ትምሕርት ሚኒስቴር ያቀደዉ የማካካሻ ትምሕርት እንዲሳካ የለጋሽ ወገኖችን ድጋፍ ጠይቋልም።ኢትዮጵያ ዉስጥ አምናና ዘንድሮ በየአካባቢዉ በተደረጉ ግጭቶችና በደረሱ ጥቃቶች በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተገድሏል፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለዉ በትንሽ ግምት ከ2.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተፈናቅሏል።

 ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ