1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማእከላዊ መዘጋቱ ተዘገበ

ዓርብ፣ መጋቢት 28 2010

የሥቅየት ተግባር ይፈጸምበታል የሚባለውና በተለምዶ ማዕከላዊ በሚል የሚጠራው እስር ቤት መዘጋቱን አሶሺየትድ የዜና ምንጭ ለመንግሥት ቅርበት ያለው መገናኛ ዘዴን ጠቅሶ ዘገበ። በማዕከሉ የነበሩ እስረኞች ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውም ተጠቅሷል።

https://p.dw.com/p/2vdLr
Symbolbild Guantanamo
ምስል picture-alliance/dpa/M. Shephard

የሥቅየት ተግባር ይፈጸምበታል የሚባለውና በተለምዶ ማዕከላዊ በሚል የሚጠራው  እስር ቤት መዘጋቱን አሶሺየትድ የዜና ምንጭ ለመንግሥት ቅርበት ያለው መገናኛ ዘዴን ጠቅሶ ዘገበ። በማዕከሉ የነበሩ እስረኞች ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውም ተጠቅሷል። ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾች እንዲሁም ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በማዕከላዊ ይገኙ ከነበሩት ውስጥ ይጠቀሳሉ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንሥትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ማዕከላዊ ተዘግቶ ቤተ-መዘክር እንደሚኾን ከሦስት ወራት በፊት  መናገራቸው ይታወሳል። በወቅቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በማዕከላዊ ምትክ «ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የምርመራ ማዕከል» በተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ መቋቋሙን ተናግረው ነበር። አዲሱ ጠቅላይ ሚንሥትር ዶክተር አቢይ አሕመድ በበኩላቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዓለ-ሢመት ንግግራቸው ወቅት «በርካታ ችግሮችን» እንደሚቀርፉ ገልጠዋል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ