1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

« ማሬ ኖስትሩም» እና የባህር ላይ ስደተኞች እጣ ፋንታ

ማክሰኞ፣ መስከረም 27 2007

ባለፈዉ ዓመት መስከረም 23 ቀን በላምፔዱዛ አቅራቢያ አንድ የስደተኞች ጀልባ ሰምጦ 366 አፍሪቃውያን፣ በብዛትም ኤርትራውያን ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/1DRjV
Italien Flüchtlinge gerettet 8.6.2014
ምስል picture alliance/dpa

ኢጣልያ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በባህር ኃይሏ ባቋቋመችው « ማሬ ኖስትሩም» በተባለው ግብረ ኃይል አማካኝነት የመስመጥ አደጋ ያሰጋቸውን ስደተኞች የማዳን ሥራ እያከናወነች ትገኛለች። ግብረ ኃይሉ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ 91 ሺ በላይ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ቢችልም ከ 3000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች አሁንም ባህር ላይ ህይወታቸዉን አጥተዋል። ይኼው የሟቾች ቁጥር ግብረ ኃይሉ በታቀደው መሠረት በቅርቡ ሥራውን የሚያጠናቅቅ ከሆነ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል የሚል ስጋት አለ። በየቀኑ ወደ አውሮፓ ስለሚጓዙት ስደተኞች እጣ ፋንታ እና ማሬ ኖስትሩም ቀጣይ ይዞታ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ