1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማሊ ከ G5 ራስዋን አገለለች

ሰኞ፣ ግንቦት 8 2014

ማሊ ጂሃዲስቶችን ከሚዋጋው (G5) ከሚታወቀዉ የሳህል ሀገራት ጥምረት እና የዓለም አቀፍ ጥምር ጦር ኃይል ቡድን ራስዋን ማግለልዋን ገለፀች። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ 2014 ዓ.ም ማሊ ሞሪታንያ፤ ቡርኪናፋሶ፤ ኒጀር እና ቻድ ተባብረዉ ጂ 5ን በመመስረት በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓ.ም ጥምር ጦር ማቋቋማቸዉ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/4BNWq
Mali Kati | Armee Soldaten
ምስል Mohamed Salaha/AP Photo/picture-alliance

ማሊ ጂሃዲስቶችን ከሚዋጋው (G5) ከሚታወቀዉ የሳህል ሀገራት ጥምረት እና የዓለም አቀፍ ጥምር ጦር ኃይል ቡድን ራስዋን ማግለልዋን ገለፀች። ማሊ ራስዋን ከአምስቱ የሳህል አካባቢ ሃገራትና ከዓለም አቀፍ ጥምር ጦር ህብረት መዉጣትዋን ያስታወቀዉ መዲና ባማኮ የሚገኘዉ ወታደራዊ ኃይል ነዉ። የማሊ ወታደራዊዉ ኃይል ከቡድን 5 ለመዉጣት የወሰነዉ ማሊ ከአምስቱ የሳህል አካባቢ ሃገራት ሌላ ሃገሪቱ የዉጪ ሃገሮች መሳርያ ሆናለች በሚል ክስ ነዉ። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ 2014 ዓ.ም ማሊ ሞሪታንያ፤ ቡርኪናፋሶ፤ ኒጀር እና ቻድ ተባብረዉ ጂ 5ን በመመስረት በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓ.ም ጥምር ጦር ማቋቋማቸዉ ይታወሳል። ይህ የማሊ ከ ጂ 5 ማለት ከአምስቱ የሳህል አካባቢ ሃገራት ጥምረት መዉጣት የተሰማዉ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር እና በፈረንሳይ መካከል ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ባለበት ወቅት ነው።

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ