1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መፍትሄ ያላገኘው የግሪክ ብድር

ዓርብ፣ ሰኔ 12 2007

ሪክ የዓለም የገንዘብ ድርጅት IMFን ለመሳሰሉ አበዳሪዎች እስከ ዛሬ 11 ቀን ድረስ መመለስ የሚገባትን ብድር መክፈል መቻሏ እያጠያየቀ ነው ።ግሪክ በተቀመጠው ቀነ ገደብ እዳዋን ካልከፈለች ከዩሮ ተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓ ህብረት ጭምር ልትወጣ እንደምትችል በሰፊው መነገሩ ቀጥሏል ።

https://p.dw.com/p/1Fjre
Luxemburg Yanis Varoufakis und Christine Lagarde
ምስል Reuters/F. Lenoir

[No title]

የዩሮ ተጠቃሚ አባል ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ትናንት በግሪክ ብድር ጉዳይ ላይ ሉክስምበርግ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ በግሪክና አበዳሪዎቿ መካከል የተፈጠረውን ልዩነትና ውዝግብ ሳይፈቱ ተለያይተዋል ። መፍትሄ ባላገኘው በዚሁ የግሪክ ጉዳይ ላይ የዩሮ ተጠቃሚ አባል ሃገራት መሪዎች እንዲወያዩ ለፊታችን ሰኞ ብራሰልስ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል ። ለሰኞ የታቀደው ይህ ስብሰባ ውጤት ማስገኘቱ እንደሚያጠራጥር እየተነገረ ነው ።ግሪክና አበዳሪዎቿ ለግሪክ የታሰበው ገንዘብ በሚሰጥበት ቅድመ ግዴታ ላይ እስካሁን ያካሄዱት ድርድር መቋጫ ባለማግኘቱ ለግሪክ ተመድቦ ከነበረው የእርዳታ ገንዘብ ቀሪው 7.2 ቢሊዮን ዩሮ እንደታገደ ነው ።በዚህ የተነሳም ግሪክ የዓለም የገንዘብ ድርጅት IMFን ለመሳሰሉ አበዳሪዎች እስከ ዛሬ 11 ቀን ድረስ መመለስ የሚገባትን ብድር መክፈል መቻሏ እያጠያየቀ ነው ።ግሪክ በተቀመጠው ቀነ ገደብ እዳዋን ካልከፈለች ከዩሮ ተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓ ህብረት ጭምር ልትወጣ እንደምትችል በሰፊው መነገሩ ቀጥሏል ።የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ