1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መጽሃፍ ትዕይንት በፍራንክፈት

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 6 2003

በአለም እጅግ ትልቅ ስለ ሚባለዉ ስለ ፍራንክፈርቱ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ፣ እንዲሁም ሰባኛ አመት የትዉልድ ቀኑ ታስቦ ስለዋለዉ ስለ ታዋቂዉ የቢትልስ የሙዚቃ ባንድ አባል ስለ ጆን ሌነን አልናስደምጥ የያዝነዉ ርእሳችን ነዉ

https://p.dw.com/p/Pe9i
ምስል DW

እዚህ በጀርመን በፍራንክፈርት ከተማ በየአመቱ የሚካሄደዉ የመጽሃፍ አዉደ ርእይ ከአለም እጅግ ግዙፍ የመጽሃፍ አዉደ ርእይ እንደሆነ ይነገርለታል። የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ በያመቱ የተለያዩ አገሮች ባህልን እና ወግን እንዲሁም ሌላ የህብረተሰብ ክንዉንን የሚያንጸባርቁ የጽሁፍ ስራዎች በማምጣት ለአለም አንባብያን ያስተዋዉቃል። ይህ በየአመቱ ለአምስት ቀናት የሚዘልቀዉ የመጽሃፍ ትርኢት ከተለያዩ አገሮች የተለያዩ የስነጽሁፍ ስራዎች በትርኢቱ ላይ ያቅርብ እንጂ በየአመቱ አንድ አገር በልዪ እንግድነት በመቅረብ አገሪቱ ያላትን ስነ-ጽሁፍ በበለጠ በማቅረብ አገሪቷ ያላትን ገጽታ ያስተዋዉቃል ባለፈዉ አመት በዚህ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ ቻይና ዋና ተጋባዥ እንግዳ ሆና መቅረቧ የሚታወስ ሲሆን በዘንድሮዉ አዉደ ርዕይ አርጀንቲና ዋነኛ ተጋባዥ እንግዳ በመሆን በስነ-ጽሁፍ ረገድ ያላትን ችሎታም ሆነ ፍላጎት አሳይታለች።
ባለፈዉ ሳምንት ለአምስት ቀናት የዘለቀዉ የፍራንክፈርቱ የመጽሃፍ ትርኢት ዘንድሮ ለስድሳ ሁለተኛ ግዜ የተካሄደ ሲሆን ከ111 አለም አገራት የተሰባሰቡ ከሰባት ሽህ አምስት መቶ የሚበልጡ አሳታሚ ድርጅቶች እና የመጽሃፍ አቅራቢዎች በትርኢቱ ተካፍለዋል። Cultura en Movimiento የባህል ልዉዉጥ ወይም ባህላዊ እርምጃ በሚል መርህ ዘንድሮ በፍራንክፈርቱ የመጽሃፍ ትርኢት ላይ የአርጀንቲና ታሪክ እና በአሁኑ ወቅት ስላለዉ እዉነታ ስነ-ጽሁፎች ቀርበዋል። ለምሳሌ የነጻነት ንቅናቄ በአርጀንቲና ፣ እንዲሁም እ. አ 1976 እስከ 1983. አመተ ምህረት ድረስ በአገሪቷ ስለነበረዉ የአንባገነን መንግስት የተለያዩ ጽሁፍች ታይተዋል። በአጠቃላይ በትርኢቱ 60 አርጀንቲንያዊ ደራስያን የአገራቸዉን ገጽታ በስነ-ጽሁፍ ለአለም አስተዋዉቀዋል። ዘንድሮ አርጀንቲና በአለም የመጽሃፍ ትርኢት ላይ መቅረብ ልዩ የሚያደርገዉ አርጀንቲና ነጻነትዋን ያገኘትበት ሁለት መቶኛ አመት የምታከብርበትም አመት በመሆኑ ነዉ። ሌላዉ ሰባኛ አመት የትዉልድ ቀኑ ታስቦ ስለዋለዉ ስለ ታዋቂዉ የቢትልስ የሙዚቃ ባንድ አባል ስለ ጆን ሌነን ዝግጅት ይዘናል ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ