1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መገናኛ ብዙሃንና የአከባቢ ጥበቃ በኢትዮዽያ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 15 2002

የአከባበ ጥበቃና የመገናኛ ብዙሃን ተዛምዶን የተመለከተ ዓለም ዓቀፍ ጉባዔ ተጀመረ።

https://p.dw.com/p/O02Y

የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች፤ጋዜጠኞች፤ የአከባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች፤ ከአከባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችን የሚያንቀሳቅሱ ዓለም ዓቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች የተካፈሉበት ጉባዔ በጀርመን ቦን ከተማ ተጀምሯል።ዶቸቬሌ ያዘጋጀው ይህ ጉባዔ የዓየር ለውጥና መገናኛ ብዙሃን በሚል ርዕስ ነው የሚካሄደው። ለ3 ቀናት በሚካሄደው በዚሁ ጉባዔ ላይ ኢትዮዽያን የተመለከተ የግምሽ ቀን የውይይት ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህም የመገናኛ ብዙሃን ሚና በኢትዮዽያ የአከባቢ ጥበቃ ዙሪያ ያለው ገፅታ ተቃኝቷል። በፕሮግራሙ ላይ የጀርመን የተፈጥሮና ብዘሃ ህይወት ጥበቃ ድርጅት በኢትዮዽያ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በተዛማጅነት ውይይት ተደርጎበታል። የኢትዮዽያ የአከባቢ ጥበቃ ጋዜጠኞች ማህበርም በኢትዮዽያ ያለውን ገጽታ ለፕሮግራሙ ተሳታፊዎች አቅርቧል።

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ