1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው ረቂቅ ህግ መጽደቅ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለረጅም ጊዜ ሲያወዛግብና ሲያጨቃጭቅ የቆየውን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣውን ረቂቅ ህግ ዛሬ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀው።

https://p.dw.com/p/GT2N
ከኤድስ ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የሚረዳ የሚስዮናውያን ድርጅት
ከኤድስ ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የሚረዳ የሚስዮናውያን ድርጅትምስል AP Photo

ወኪላችን ታደሰ እንግዳው እንደዘገበው፡ ምክር ቤቱ ባለፈው ህዳር ሀያ ሶስት ቀን በረቂቅ አዋጁ ላይ ከመከረበት በኋላ ለዝርዝር እይታ ለህግና አስተዳደር፡ እንዲሁም፡ ለማህበራዊና ለውጭ መከላከያና ደህንነት ጉዳይዮች ቋሚ ኮሚቴዎች መርቶት ነበር። በምክር ቤት የተወከሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደራሴዎች ረቂቁ ህግ አሁንም ጉድለት አለው በሚል አልደገፉትም።