1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መስከረም 20 ከ7.6 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምጽ ይሰጣሉ ተባለ

ሰኞ፣ መስከረም 10 2014

በሦስት ክልሎች ውስጥ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ 7 ሚሊዮን 686 ሺህ 549 መራጮች መመዝገባቸው ተገለፀ። በደቡብ ክልል በአምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔም ሆነ የምርጫው ውጤት እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ. ም ድረስ ይገለፃል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/40Zl1
Äthiopien | NEBE | Soliana Shimelis
ምስል Solomon Muchie/DW

መስከረም 20 ከ7.6 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምጽ ይሰጣሉ ተባለ

በሦስት ክልሎች ውስጥ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ 7 ሚሊዮን 686 ሺህ 549 መራጮች መመዝገባቸው ተገለፀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ምርጫ ባልተደረገባቸው የሶማሌ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም ሐረሪ ክልሎች 47 የተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች እና 105 ለክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ክልሎች ድምጽ ይሰጣል። 22 የፖለቲካ ፓርቲዎችም በምርጫው ይሳተፋሉ ተብሏል። በደቡብ ክልል በአምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔም ሆነ የምርጫው ውጤት እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ. ም ድረስ ይገለፃል ተብሏል።

ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ