1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መምህር የኔሰውና አሟሟቱ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 12 2004

ከአንድ ሳምንት በፊት ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ- ዋካ ዞን፣ የአስተዳደር መሻሻል እንዲደረግ ይጠይቁ ከነበሩ የአካባቢው ተጠሪዎች መካከል፣ አቶ የኔሰው ገብሬ የተባለው የ 29 ዓመት ወጣት መምህር ፤ ራሱን ቤንዚን አርከፍክፎ በማቃጠል ፤ ህይወቱ ካለፈች ወዲህ በአካባቢውና በተለያዩ የውጭ ሀገራት በሚኖረው

https://p.dw.com/p/Rxt5

የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ዘንድ ፣ የዚህ ሰው አስደንጋጭ ኅልፈተ- ህይወት ማነጋገሩን ቀጥሏል።
ሟቹን በህይወት ሳለ ከቅርብ የሚያውቁትን ማግኘት ባያዳግተንም ፤ በተጨማሪ የአካባቢውን ባለሥልጣናት አነጋግረን ለማቅረብ በተደጋጋሚ እስከዛሬ ድረስ ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም። ተክሌ የኋላ ፣ መምህሩንና የአካባቢውን ችግር በሚገባ ጠንቅቀው ያውቃሉ ከሚባሉ መካከል ፤ 2 ሰዎች አነጋግሮ የሚከተለውን አጠናቅሯል።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ