1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብ

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 6 ከትዕይንት 1 እስከ 4)

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2010

ወንጀል ተፋላሚዎቹ! አዲስ ተከታታይ ድራማ ጽሑፍ በፌስ ቡክ። በፈጣን የሴራ ፍሰት፥ በአጫጭር ትእይንቶች የተገነባው ድራማ በአይነቱ ለየት ያለ ነው። ይኽ የድራማ ጽሑፍ በዶይቸ ቬለ የአማርኛው ክፍል የፌስቡክ ገፅ የሚቀርብ ሲኾን፤ ለሽልማት የሚያበቃ ነው። ስለ ተሳትፎ እና ውድድሩ ፌስቡክ ገጻችን ላይ በዝርዝር ይገኛል።

https://p.dw.com/p/2h8LH
09.2015 Crime Fighters MQ amharisch

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 6 ትዕይንት 1)

ባለፈው ትረካ መርማሪ ዓለሙ የአንድ ዉስብስብ ወንጀል ምሥጢርን ለመፍታት ጥረት ላይ ነበር፡፡ የጓደኛው የጳዉሎስን ገዳይ ለማግኘት በጀመረው ምርመራ ወደ ዉጤት እየተጠጋ ሲመስለው ነገሮች በዛው መጠን እጅግ እየተወሳሰቡ ሲሄዱ ተከታትለናል። በሌላ በኩል የዓለሙ ጓደኛ ከበደ ስኬት አስመዝግቧል፡፡ እሱ እና የእርሱ ቡድን ሁለት ሕገ-ወጥ አዳኞችን ይዘዋል፡፡ ሕገ-ወጥ አዳኞቹ የቡድናቸዉ መሪ ወደ ሆነው ወደ ሚስተር ጂ ይመሩት ይሆን?  ለመሆኑ ሚስተር ጂስ ማንነው? ወንድ ወይንስ ሴት? በርካታ ሰዎች ተሰብስበዋል። ዶ/ር ሰናይት ንግግር እያደረጉ ነው።

«ዛሬ እዚህ የታደምነው ከባቢ ጉዳይ  ያገባናል፤ ቁጥራቸው በመናመን ላይ ያለው የእነዛ የምስኪን ዝኖች እና አውራሪሶች ጉዳይ ያገባናል ብለን ነዉ»

«ትክክል ነው ያገባናል!»

«እነዚህ ምስኪን እንስሳት በእነዚያ ጨካኝ እና ስግብግቦች መጨፍጨፍ፤ ጥርስና እና ቀንዶቻቸው መወላለቁም ማክተም አለበት! ዛሬ እዚህ የተሰበሰብነው ይኽንኑ ድጋፋችንን ለመግለጽ ነው!»

«አዎ፤ ሁላችንም ተቆርቋሪዎች ነን! ሁላችንም ያገባናል!»

ዶ/ር ሠናይት ንግግር በሚያደርጉበት ቅጽበት የዝግጅቱ አስተባባሪ የአጭር መልእክት በስልኩ ይደርሰዋል። መልእክቱ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የተላከ ነው።

«ይቅርታ! ዶ/ር ሰናይት!  ይኽን ጉዳይ ቀደም ብለው ይወቁት አይወቁት እርግጠኛ ባልሆንም ... አሁን አንድ መልእክት ደርሶኛል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ለዱር እንስሳት እና ቱሪዝም ግብረ-ይል አዲስ ሊቀ-መንበር ሾመዋል! እናም አዲሷ ሸመኛ የእኛዋ ክብርት ዶ/ር ሰናይት ናቸው!»

ተሰብሳቢው በደስታ ተውጦ ያጨበጭባል።  ሁለቱ መርማሪ ፖሊሶች ዓለሙ እና ከበደ ጣቢያው ውስጥ ከምሳ በኋላ ተገናኝተዋል።  ከበደ ስላገኘው አንድ ትልቅ ስኬት ለሥራ ባልደረባዉ ለመንገር ቸኩሏል!

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 6 ትዕይንት 2)

ሕገ-ወጥ አዳኞቹ በቁጥጥር ስር ቢውሉም ሚስተር ጂ የሚባለው መሪያቸው ዱካ ግን አሁንም ሊገኝ አልቻለም። ሕገ-ወጥ አዳኞቹ ስለ ሚስተር ጂ የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆን? መርማሪ ፖሊስ ከበደ ትናንት ማታ ስለመሸበት ዛሬ በጥያቄ ሊያፋጥጣቸው ዝቷል። የመርማሪ ዓለሙ ክትትልስ ከምን ደረሰ?

«የእኛ ምርመራ ምንም ለውጥ የለውም። ለሚስተር ጂ የማስፈራሪያ መልእክቱን  የላከለት ሰው  ሟቹ ጳዉሎስ ይሁን ወይስ ሌላ ሰው በትክክል ማወቅ አልቻልኩም።»

«ሉሲስ?»

«ሉሲም ብትሆን ባሏ ከሌላ ሴት ጋር ይማግጥ አይማግጥ ምንም የምታውቀው ነገር እንደሌለና የሚስተር ጂ ማንነትን በተመለከተ ምንም የምታውቀው ነገር እንደሌለ ተናግራለች። ጳውሎስም ስሙን ሲያነሳ  ሰምቼ አላውቅም ነው ያለችው።»

«እህ ቅናት የወለደው ወንጀል!»

«እሷ የፈጸመችው እንኳን አይመስለኝም። ምናልባት የጳውሎስ ውሽማ የነበረችው ቤቲ? ጳዉሎስ ሊተዋት ነበረ፡፡ የቴክኒክ ምርመራ ክፍሎ የቤቲ የጣት አሻራ በጳዉሎስ ኮምፒዉተር ላይ እንደተገኘ ነግረውል፤ እብትሆን ማስተባበያ አላቀረበችም።»

«ዓለሙ፤ የያዝከው ጉዳይ ትንሽ ወሰብሰብ ያለ ይመስላል። ለማንኛውም አንተ ቀጥል ማን ያውቃል … ምናልባት ሕገ-ወጥ አዳኞቹ ስለ ሚስተር ጂ እና የማስፈራሪያ መልዕክቱን ስለላከለት ሰው ፍንጭ ሊሰጡን ይችሉ ይሆናል!»

«እኔም እንደዛ ነው የማስበው!»

ሕገ-ወጥ አዳኞቹ እስር ቤት እንደተከረቸመባቸው ሚስተር ጂን የማደኑ ሥራ ተጧጡፏል! አስታውሱ፤ ለሚስተር ጂ የዛቻ መልዕክቱን ሲልክለት የነበረው ግለሰብ የእርሱን ትክክለኛ ማንነት የሚያሳየውን የቪዲዮ ምስል ይፋ ለማውጣት ዝቷል፡፡ ቀጥሎ የምናገኛት ደግሞ ሙናን ነው። ከታላቅ ወንድሟ ከጳዉሎስ ሀዘን ገና አልተነሳችም።»

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 6 ትዕይንት 3)

ሙና የታላቅ ወንድሟ ጳዉሎስ ግድያ ቅስሟን እንደሰበረው ገና ከሀዘን ላይ አልተነሳችም። የእጅ ስልኳ ይጠራል።

« ሎ ዮዲት?»

« ሀይ! ሙና ተኝተሻል እንዴ?»

«አያይ ዝም ብዬ ሶፋዉ ላይ  ጋደም ብዬ ነው።»

«ሙናዬ ቆይ አንቺ ግን ወደ ሥራ የምትመለሺው መቼ ነው? ናፍቀሽናል እኮ»

«እምም…ያው» በስልኩ ውስጥ የዮዲት ቴሌቪዥን ድምፅ ሲጨምር ጎላ ብሎ ይሰማል።

«እንዴ ቆይ ቆይ ሙናዬ ቶሎ በይ ቴሌቪዝኑን ክፈቺው! ቶሎ በይ እንዳያመልጠሽ። ስለ ጳውሎስ»

ሙና በፍጥነት ቴሌቪዥኗን ትከፍታለች። ቪዲዮው እየተጫወተ ጋዜጠኛው በማውራት ላይ ነው።

«ይህ የምትመለከቱት የቪዲዮ ምስል ለጣቢያችን የደረሰው በምሥጢር ነው።»

«ምን?ሙና ትንፋሿ ይቆራረጣል። የምትመለከተውን ማመን አልቻለችም።

በምስሉ ውስጥ ሕገ ወጥ አዳኞች የዱር እንስሳትን ሲጨፈጭፉ ይታያል። ጋዜጠኛው ንግግሩን ይቀጥላል። «የሕገ-ወጥ አዳኞ መሪ ሚስተር ጂ በመባል የሚታወቀው የተደራጁ ወንጀለኞች መሪ የሆነው ግለሰብ፤ በቦቩ ውስጥ ዝነኛና ታዋቂ ከሆኑት ሰዎች መካከል አንዱ መሆኑ መጋለጡ በጣም አስደንጋጭ ወሬ ኾኗል» የቲቪ ስርጭቱ ይጠናቀቃል። 

«ምን?ሙና ከድንጋጤዋ አሁንም አልተላቀቀችም 

«ሚስተር ጂ ሲባል የነበረውእኔ ይኼን አላምንም።»

«አይዞሽ ሙናዬ»

«የምራቸውን ነው ግን? ይሄንን ለዓለሙ መንገር አለብኝ!» ስልክ መደወል ትጀምራለች።

እና በዚህ መክሉ ሌላኛው ጉድ ተጋላጠ፡፡ ወደ ቦቩ ዩኒቨርሲቲ ስናቀና ደግሞ፤ ባተሌዋን

የዱር እንስሳት ተንከባካቢ ዶ/ር ሰናይት ዕውቀቷን ለተማሪዎች ስታካፍል እናገኛታለን፡፡

*** 

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 6 ትዕይንት 4)

የሚስተር ጂ ማንነት አሁንም እንቆቅልሽ እንደኾነ ነው፤ በዚህ ድብቅ ስም የሚንቀሳቀሰው ግለሰብ ወንድ ይሁን ሴት ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። የዱር እንስሳት ተንከባካቢዋ ዶ/ር ሰናይት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስለ ሕገወጥ አዳኞች እና በሚስተር ጂ መሪነት ስሚጨፈጨፉ እንስሳት ንግግር እያደረጉ ነው።

«ለማንኛውም  ዛሬ የመጣሁት ስለ ሥራዬ ጥቂት ገለጻ እንድሰጣችሁ ተጋብዤ ነው….ሁላችሁም እንደምታውቁት ሥራዬ የዱር እንስሳትቶችን፤ ዝኆኖችን፣ አውራሪሶችን  እና ሌሎች የዱር ፍጥረታትን መንከባከብ ነው። ሥራዬ በየቦታው ዝም ብሎ መለፍለፍ ብቻ ሳይሆን…»

ተማሪዎቹ ይስቃሉ።  ከውጭ በሩ ድንገት ይበረገዳል።  ገነት እያለከለከች በፍጥነት ወደ ክፍሉ ትገባለች።

«ይቅርታ ዶ/ር ሰናይት….»

ዶ/ር ሰናይት ግራ በመጋባት ገነትን ይመለከታሉ «ምንድነው ገነት?»

«በፍጥነት አሁኑኑ መሄድ ይኖርብናል!»

«ክፍል ውስጥ ገለፃ የእየሰጠሁ መሆኔን እያየሽ አይደለም እንዴ?»

«አሁኑኑ መሄድ ይኖርብናል»

ዶ/ር ሰናይት ተማሪዎቹን በፈገግታ እየተመለከቱ ግን ደግሞ ትንሽ ስጋት ገብቷቸው ይናገራሉ።

«ይቅርታ! ለአስቸኳይ ጉዳይ ፈልገውኝ መሰለኝ! ደረስ ብዬ እመጣለሁ» ከገነት ጋር ተያይዘው ይወጣሉ። ተማሪዎቹ ማጉረምረም ይጀምራሉ።

«እንዴ? ኧረ ጉድ! ሚስተር ጂ ማለት ይህቺ ነች? ጉድ በል አለ ያገሬ ሰው!»

በስተመጨረሻ የሚስተር ጂ ማንነት ተጋለጠ! የሚስተር ጂ  ማንነትን ማወቅ ከፈለጋችሁ የሚቀጥለውን ክፍል ይጠብቁ።  

***

 

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 1 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 2 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 3 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 4 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 5 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 7 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 8 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

ጀምስ ሙሃንዶ

ማንተጋፍቶት ስለሺ