1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለ3,2 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ መጠየቁ፤

ረቡዕ፣ ጥር 16 2004

በአፍሪቃዉ ቀንድ 13,3 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ የመጠለያ፤ እና ሌሎች እርዳታዎች እንደሚያስፈልገዉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ማመልከታቸዉን አሶሲየትድ ፕረስ ከዋሽንግተን ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/13ppj

በተጠቀሰዉ አካባቢ በተለይ በሶማሊያ የታየዉ አስጊ የረሃብ ሁኔታ መታገሱንም ዘገባዉ አመልክቷል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ደግሞ በግብርናና ገጠር ልማት ሚንስቴር የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ፤ የምግብ ዋስትና ዘርፍ፤ ከተባበሩት መንግሥታት ፣ ለሕጻናት የአስቸኳይ ሁኔታ እርዳታ አቅራቢው ድርጅት (UNICEF) ጋር በኅብረት፤ ለ 3,2 ሚሊዮን የረሃብ ተጠቂዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል ሲሉ በጋራ ጥሪ አቅርበዋል።

ጌታቸው ተድላ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ