1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለፌዴራል ጠቅላይ ም/ ቤት ዳኞች መሾማቸዉ

Merga Yonas Bulaሰኞ፣ ሰኔ 20 2008

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሳለፍነዉ ሃሙስ 111 ዳኞች ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሾማቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ለሹመቱ ወደ 3000 አመለካቾች እንደተወዳደሩ እና የማጣራት ሂደትም ከአንድ ዓመት በላይ እንደወሰደ ተዘግበዋል።

https://p.dw.com/p/1JEY0
Äthiopien Parlament Hailemariam Desalegn
ምስል DW/Y. G. Egziabher

[No title]

በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 81 ንዑስ አንቀፅ አንድ እና ሁለት መሰረት የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ዳኞቹ በሕግ ትምህርት የሰለጠኑ ወይም የህግ ልምድ እና እዉቀት ያላቸዉ፣ ለህገ መግስቱ «ታማኝ» የሆኑ እንዲሁም «በታታሪነት፣ በፍትሕዊነት፣ በሥነ-መግባራቸዉ መልካም ስም ያታረፉ»፤ እድሜያቸዉ ከ25 ዓመት በላይ የሆኑትና በዳኝነት ለመስራት ፍቃደኛ የሆኑ እንደታጩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የእንፎርመሸን ኮሙኒከሸን ዳይሬክቶረት ዳይሬክቴር ወዘሮ አፀዱ ረጋሳ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።


የቀድሞ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ተገነ ጌታነህ በጤና ምክንያት ከስራ ቦታ እንደለቀቁ እና ምክትላቸዉ አቶ ሜዲን ኪሮስ ደግሞ በዓመቱ መጨረሻ ጦረታ እንደምወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።


የአገሪቱ የሕግ አስፈፃሚ አካል በፍትህ ስረዓቱ ዉስጥ ጣልቃ ሥለሚገባ ዜጎች በፍትህ እጦት ተበድለዋል ሲሎ አስተያየታቸዉን የሚሰጡ አሉ። ስለዝህ አድስ ዳኞች መሾም የእጅ ጉዋንት መቀየር ካልሆነ በፍትህ ስራዓቱ ላይ ለዉጥ እንደማያመጣም አስተያየታቸዉን ያንፀባርቃሉ።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ