1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለዳርፉር ውዝግብ የተደረሰው የተኩስ አቁም ደምብ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 9 1996

በምዕራባዊው የሱዳን ከፊል በሚገኘው የዳርፉር አካባቢ በሚንቀሳቀሱት ሁለት ያማፅያን ቡድናት፡ ማለትም በሱዳን ነፃ አውጪ ጦርና በፍትሕና እኩልነት እንቅስቃሴ፡ እንዲሁም በሱዳን ማዕከላይ መንግሥት መካከል እአአ ባለፈው ሚያዝያ ስምንት የተደረሰው የአርባ አምስት ቀናት የተኩስ አቁም ደምብ አሁን ተግባራዊ ሆኖዋል። ይህንኑ ሂደት የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደ መልካም የመጀመሪያ ርምጃ ቢያዩትም፡ በወቅቱ በቦታው የሚታየው ገሀዱ ሁኔታ ብዙም ተስፋ የሚያስደርግ

https://p.dw.com/p/E0l1
ምዕራብ ሱዳናውያን ስደተኞች
ምዕራብ ሱዳናውያን ስደተኞችምስል AP

��ንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ፀንቶ መቆየቱ አብዝቶ በሚያጠራጥረው የተኩስ አቁሙ ደምብ መሠረት፡ ተቀናቃኞቹ ወገኖች ለውዝግቡ ዘላቂ መፍትሔ ለማፈላለግ ከሁለት ሣምንታት በኋ ተገናኝተው ለመደራደር ላካባቢው የሰብዓዊ ርዳታ የሚገባበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እዚያው ሱዳን ውስጥ የሚገኙትና ወደ ሌላ ሀገር የተሰደዱ የዳርፉር አካባቢ ነዋሪዎች ሁሉ በውዴታ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው የሚመለሱበትን መንገድ ለማስተካከል ተስማምተዋል። ከዚህ በተረፈም፡ የሱዳን መንግሥት ዐረባውያኑ ሚሊሺያዎች በዳርፉር ሲቭል ሕዝብ፡ በተለይም በፉር እና በማሳሊት ጎሣ አባላት፡ እንዲሁም በዲንካ ጎሣም ጭምር ላይ የሚፈፅሙትን አስከፊውን ጥቃት ለማስቆም ቃል ገብቶዋል። ይሁን እንጂ፡ በሰሜን ሱዳን የሚኖሩት ዐረባውያኑ ዘላኖች ያቋቋሙትንና ለጥቃቱ ተጠያቂ የሆኑትን የዣንዣዌድ ቡድን ሚሊሺያዎችን እንዴት ትጥቅ ማስፈታት የሚቻልበት ሁነኛ ዕቅድ ባለመውጣቱና ሚሊሺያዎቹም የስምምነቱ ተፈራራሚዎች ባለመሆናቸው የተኩስ አቁሙ ደምብ መፅናቱን ብዙዎች ተጠራጥረውታል። የዩኤስ አሜሪካ መንግሥት ከጥቂት ጊዜ በፊት እንዳስታወቀው፡ የዣንዣዌድ ሚሊሺያዎች የተኩስ አቁሙ ደምብ ከተደረሰ በኋላ በሁለት የዳርፉር መንደሮች ጥቃት ማካሄዳቸውን የሚገልፁ ዘገባዎች አግኝቶዋል።
ይኸው የሚሊሺያ ቡድን በዳርፉር ጥቁር አፍሪቃውያን ነዋሪዎች ላየሚፈፅመው የግድያ፡ የዝርፊያ፡ መንደሮቻቸውን የማቃጠል፡ እንዲሁም፡ ሴቶችንና ወጣት ልጃገረዶችን ክብረ ንፅሕና መድፈርን፡ ወዘተ የመሳሰሉት ወንጀሎች የተነሣ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ነው ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለው፡ ሌሎች አሥር ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ወደ ጎረቤት ቻድ ተሰደዋል፡ የሱዳን መንግሥት የሰብዓዊ መብትን በማያኣኣኣኣከብርበትና ረሀብን እንደ መሣሪያ በሚጠቀምበት ድርጊትም ሰበብ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ የረሀቡ አደጋ አሥግቶታል። የሱዳን ማዕከላይ መንግሥትና ያካባቢ መስተዳድር ባለሥልጣናት ከዐረባውያኑ የዣንዣዌድ ቡድን ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው በተደጋጋሚ ቢያስታውቁም፡ በምዕራባዊው ሱዳን በመንግሥቱ ጦር አንፃር ለሚዋጉት ያማፅያን ቡድኖች ጥቁሮቹ ያካባቢው ነዋሪዎች በአባልነትና ርዳታ በማቅረብ ይረዳሉ የሚላቸውን ያካባቢውን ነዋሪዎች የዣንዣዌድ ሚሊሺያዎች ካካባቢው እንዲያባርሩለት የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ መለዮ በማልበስና የጦር ሥልጠና በመስጠት ይረዳል፡ የግጦሽ መሬትና ውኃ ፍለጋ ወደ ደቡቡ የሄዱትም የዣንዣዌድ ሚሊሺያዎችም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይወቅሱታል። ሚሊሺያዎቹ በዳርፉር ሲቭል ሕዝብ አንፃር የሚፅሙትን አሰቃቂ ወንጀል ባካባቢው የሚሠሩትና የሱዳን መንግሥት የዳርፉርን ሕዝብ ለመርዳት የሚያደርጉትን ጥረት ሆን ብሎ እንደሚያስተጓጉለው የገለፁት የርዳታ ሠራተኞች ያረጋግጡታል። የርዳታ ሠራተኞቹ ቪዛ ለማግኘት ሣምንታት፡ አንዳንዴም ወራት መጠበቅ እንደሚገደዱ ነው ያስረዱት።
የተኩስ አቁሙ ደምብ ቢደረስም በደቡባዊ የዳርፉር ክፍለ ሀገር የሚገኙት አንድ መቶ አርባ ሺህ ተፈናቃዮች ሰብዓዊ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የተ መ ድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መሥሪያ ቤት አስታውቋል። በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ሣምንት ብቻ፡ በስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መሥሪያ ቤት ዘገባ መሠረት፡ ሀያ ሺህ ተፈናቃዮች ከገጠሩ ወደ ከተሞች ገብተዋል። ይከው ሂደትም የዣንዣዌድ ሚሊሺያዎች የሚያካሂዱትን የግድያ እና የዝርፊያ ወንጀል እስካላቆሙ ድረስ እንደሚቀጥል ነው ስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መሥሪያ ቤት ያሳሰበው። በገቲንገን የሚገኘው ሥጋት ለተደቀነባቸው ሕዝቦች የሚሟገተው የጀርመናውያኑን ድርጅት የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ከአሥር ዓመት በፊት፡ ዓለም አቀፍ ኅብረተ ሰብ እያየ ስምንት መቶ ሺህ ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበት ዓይነቱ ጭፍጨፋ በምዕራባዊው ሱዳንም እንዳይደገም አስጠንቅቀዋል።