1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለደቡብ ሱዳን ወሳኝ የተባለ የሰላም ስምምነት መፈረሙ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 23 2008

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይላት በሀገሪቱ ሰላም ለማስፈን ወሳኝ የተባለ የሰላም ስምምነት በዛሬዉ ዕለት በአዲስ አበባ ተፈራረሙ። ተቀናቃኞቹ ወገኖች ዛሬ በአዲስ አበባ የተፈራረሙት ስምምነት ሃገሪቱን በጋራ ማስተዳደር ወደሚችሉበት ሂደት ያመራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/1Gz0T
Karte Südsudan Provinz Jonglei Englisch
ምስል DW

[No title]

በኢጋድ፣ በአፍሪቃ ህብረት እና በአጋር ድርጅቶች ሸምጋይነት በተደረሰው ስምምነት መሰረት፣ ስልጣን ላይ የሚገኘዉ የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ነፃ አዉጭ ንቅናቄ SPLM፤ በዚሁ ስም የሚጠሩ ተቀናቃኞቹ SPLM (IO) ወይም ወይም ኢን ኦፖዚሽን» እንዲሁም SPLM (A) የሚባሉት ቡድኖች ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ጦርነት ለማቆም ተስማምተዋል። የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ቡድኖች፣ ኃይሎቻቸውን በማራራቅ በተለያዩ ካምፖች ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም፣ የጁባ እና የሌሎች ከተሞችን ከጦር እንቅስቃሴ ነፃ ለማድረግ እና የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችላቸዉን መንገድ ለማስተካከል ነው የተስማሙት

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ