1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአፍሪቃ ዕድገት የሳይንስና ቴክኖሎጂ አጋርነት፣

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2003

በኤኮኖሚ ልማት ወደኋላ የቀረው ደቡቡ ንፍቀ- ክበብ ፤ የተጋረጡበትን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች በመቅረፍ የዕድገት እመርታ ለማሳየት፣ አብነቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ነው።

https://p.dw.com/p/RJK9
ቴክኖሎጂና የዕውቀት ልውውጥ፣ በጀርመኑ ፍራውንሆፈር ተቋምና በዛምቢያ መካከል፤ምስል Fraunhofer FOKUS

የአፍሪቃ ኅብረት አባል ሀገራት ከ 3 ዓመት በፊት፤ ካልተጣራ ብሔራዊ ገቢያቸው ፣ ቢያንስ 1 ከመቶውን ለሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ለማዋል ተስማምተው እንደነበረ ቢታወስም፣ ተግባራዊነቱ፤ እንደስምምነቱ አለመሆኑ ነው የሚነገረው። መንስዔው ምን ይሆን? የሥነ-ቴክኒክ ዝውውር የሚሰኘውስ፣ ጠቀሜታው እስከምን ድረስ ነው? የአፍሪቃ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፤ የፈጠራና ልማት ፣ የኢንተርኔት ዓምደ- መረብ ሚና እንዴት ይታያል? የዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ዝግጅት፣ ለአፍሪቃ ዕድገት የሳይንስና ቴክኖሎጂ አጋርነት በሚል ርእስ አንድ የዘርፉን ባለሙያ ለቃለ-ምልልስ ጋብዟል።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ