«ለአዲስ አበባ ምን ይደረግ?» ስብሰባ በአዲስ አበባ
እሑድ፣ መጋቢት 1 2011ማስታወቂያ
ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ «ለአዲስ አበባ ምን ይደረግ?» በሚል የጠራው ስብሰባ ዛሬ ከቀኑ 8 ጀምሮ አዲስ አበባ ባልደራስ አዳራሽ ውስጥ ተከናወነ። በስብሰባው ስለአዲስ አበባ ጉዳይ ያገባናል ያሉ በርካታ ሰዎች በተለይ ወጣቶች ተገኝተዋል። ስብሰባው አራት የጋራ አቋም መግለጫ ነጥቦችን በማውጣት ተጠናቋል። «ሴራ ተጎንጉኖብናል፤ በመስቀል አደባባይ ላይ ትልቅ ሰልፍ እናደርጋለን» ማለታቸውን ጠቅሷል። ተስብሳቢዎቹ፦ «አዲስ አበባ በትክክል በሚወክላት ሰው መወከል ይገባታል» ማለታቸውንም በስብሰባው የታደመው የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ በቃለ መጠይቁ ገልጧል።
ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከታች ባለው ማገናኛ ማድመጥ ይቻላል።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ