1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለምን ጥራዝ ነጠቅ ቋንቋ?

ሐሙስ፣ መጋቢት 6 2004

በአገራችን አማርኛን ከእንግሊዘኛ እየደባለቀ የሚናገረዉ ህዝብ በመብዛቱ ቋንቋዉም ሆነ ባህሉ እጅግ እየተበላሽ እና መልኩን እየቀየረ መምጣቱ እጅግ አሳሳቢ ሆንዋል። አማርኛን እና እንግሊዝኛን እየቀላቀላችሁ ለምን ታወራላችሁ? ብለዉ የሚጠይቁ ሰዎች እዉን መልሱ ጠፍቶአቸዉ ነዉ? መቀላቀል ማለት ሊቅነትም አይደል? ሊቅነትን ለማሳየት ነዋ!

https://p.dw.com/p/14LHJ
ምስል Getty Images

በአገራችን አማርኛን ከእንግሊዘኛ እየደባለቀ የሚናገረዉ ህዝብ በመብዛቱ ቋንቋዉም ሆነ ባህሉ እጅግ እየተበላሽ እና መልኩን እየቀየረ መምጣቱ እጅግ አሳሳቢ ሆንዋል። በእንግሊዘኛ የመቀላቀሉ አባዜ እዉን የአማርኛ አልያም አፍ በፈታንበት ቋንቋ መጠርያ አጥተንለት ነዉን? ችግሩ ምን ይሆን ? አማርኛን እና እንግሊዝኛን እየቀላቀላችሁ ለምን ታወራላችሁ? ብለዉ የሚጠይቁ ሰዎች እዉን መልሱ ጠፍቶአቸዉ ነዉ? መቀላቀል ማለት ሊቅነትም አይደል? ሊቅነትን ለማሳየት ነዋ! ብለዉ በነገሩ ግራ የተጋቡ፣ የሁኔታዉን አሳሳቢንነት በም ጸት የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም።  አብዛኞች እንደሚሉት ቋንቋን የሚቀላቅሉ የሚናገሩበትን የአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉንም ሆነ እንጊልዘኛዉን አጥርተዉ አያዉቁትም ። ለነገሩ ሽሮም ወደድ የሚለዉ ቅቤ ጣል ሲልበት ነዉ የሚጣፍጥ እና አጥርተዉ በሚያዉቁት ቋንቋ ላይ እንግሊዘኛ ቋንቋ ጣል ማድረጋቸዉ አዋቂነታቸዉን ለማሳየት የሚያደርጉት ነዉ። እንግሊዘኛዉም ቢሆን እንደ ቅቤዉ ዉድ ሆነብን subject + verb+ object = sentence እየተባልን ሂሳብን እንጂ ቋንቋን ያልተማርን ሰዎች አሁንም  ቋንቋችን ላይ እንግልዝኛዋን ጣል ከማድረግ ባለፈ አጥርተን ለመናገር ከየት እናምጣዉ ይለናል ዲያቆን ዳን ኤል ክብርት  የነገሩን አሳሳቢነት ለማሳየት ሰምወኑን „ጣል“ በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገዉ ጽሁፉ። ዲያቆን ዳንኤል   

MStudenten auf dem Campus der Universität Addis Abeba
ምስል DW

በመቀጠል ስለ ቡና ስለ ቢራ የእግር ኳስ ተቻዋቾቻችን ብቻ አዉርተን አድማጭ ከምናጣ ስለአርሴናል ማንችስተር ማድሪደ ባርሴሎና ጣል አድርገን አድማጭ በቅጡ እንድናገኝ እንጥራለን። ለነገሩ 30 ሺ ወገኖቻችን የሰማዕታት 75ኛ ዓመት በአል ይልቅ የቫለንታይን በዓል በሚደምቅበት አገር ተቀምጠን እንግሊዘኛ ጣል አታድርጉ ማልት ነዉር አይደለምን ይላል በመጠየቅ በጽሁፉ ! የለቱ እንግዳችን ነዉ። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቋንቋ ጥናት ተቋም ዉስጥ መምህር የሆኑት አቶ ወንደሰን አዳነ ቋንቋ ቀላቅሎ መናገር በሁሉም ህብረተሰብ ያለ ቢሆንም እኛ አገር ሊታሰብበት እንደሚገባ አስረግጠዉ ይናገራሉነገሩ አሳሳቢ ደርጃ ላይ መድረሱን ይናገራሉ። መምህር ወንደሰን እንግሊዝኛን እየቀላቀልን የምናወራ ከሁለቱም ያጣ እንዳንሆን ይላሉ! ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደስ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ