አዲስ አስታራቂ ኮሚቴ
ዓርብ፣ ኅዳር 22 2010ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ እና ስደተኛው በሚል ተለያይተው ለዓመታት የዘለቁትን የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለማስታረቅ የሚሰራ አዲስ ኮሚቴ ተቋቋመ። አዲስ የተቋቋመው ይኽው ኮሚቴ በሀገር ውስጥ ካለው የቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ እና በዉጭ ሀገር በስደት ከሚገኘዉ ሲኖዶስ ድጋፍ እንዳለው የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥረት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ ቢሆንም፤ አሁን አዲስ ጥረት መጀመሩን የሚገልፀዉ አስታራቂ ኮሚቴ ሚናው ሽምግልና እንደሆነ እና አላማዉም ሁለቱን ሲኖዶሶች አንድ ማድረግ መሆኑን አስታውቋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ