ፓሪስ ጥቃቷን እያሰበች ዋለች
ሰኞ፣ ኅዳር 4 2010ማስታወቂያ
ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ስድስት ቦታዎች ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ በተገኙበት የመታሰቢያ ጉንጉን አበባ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ተካሒዷል። መንግሥታቸው መሰል ጥቃቶችን ለመከላከል ለፖሊስ እና የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች የስልክ ንግግሮችን የመጥለፍ፣ የመበርበር እና የማሰር ሰፊ ስልጣን የሰጠው ኤማኑዌል ማክሮ በመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓቱ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንትም አጅበዋቸዋል። ከሁለት አመት በፊት ለተፈጸመው ጥቃት ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ኃላፊነት ወስዷል። ፓሪስ ከአመት በኋላ ምን ትመስል ይሆን? ሐይማኖት ጥሩነህ የፓሪስ ነዋሪዎችን አነጋግራ የሚከተለውን ዘገባ ልካልናለች።
ሐይማኖት ጥሩነህ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ