ፍሬ አልባዉ የትራምፕ መልዕክት
ረቡዕ፣ ግንቦት 16 2009ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛዉ ምሥራቅ ባደረጉት ጉብኝት አሸባሪዎችን ለመዋጋት፤ ከኢራን ይሰነዘራል ያሉትን ሥጋት ለመግታት እና የእስራኤልን ደሕንነት ለማስጠበቅ «የማይናወጥ» አቋም መያዛቸዉን በየደረሱበት ተናግረዋል።አካባቢዉን ለሰባ ዓመት የሚያብጠዉን የእስራኤልና የፍልስጤምን ጠብ ለማስወገድ ሁለቱ ወገኖች እንዲደራደሩ መናገራቸዉም አልቀረም።ይሁንና እንደ ልዕለ-ኃያል ሐገር መሪ እስራኤልና ፍልስጤምን ለማስማማት የሚረዳ ምንም ነገር ሳያደረጉና ሳይሉ ከአካባቢዉ ተሰናብተዋል።የዶቼ ቬለዉ ዘጋቢ ቲም አስማን የዘገበዉን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ከበርሊን እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ