ወደ ኢትዮጵያ እንዳልገባ የተደረግሁት በኤምግሬሽን ኃላፊዎች ነው:- ሬኔ ለፎ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 12 2010ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚያቀርቧቸው ትንታኔያቸው ስማቸው ጎልቶ ይጠራል፡፡ ፈረንሳዊው ጸሀፊ ሬኔ ለፎ፡፡ ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት በፈረንሳይ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ አሁን ደግሞ በጥናት እና ምርምር ጽሁፎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሬኔ ለፎ ለበርካታ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለሱ ቆይተዋል፡፡ ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠየቁትን የስራ ቪዛ ካገኙ በኋላ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ወደ አዲስ አበባ ያመሩት ለፎ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ያልጠበቁት ነበር ያጋጠማቸው፡፡ በአየር ማረፊያ ከሚገኙ የኤምግሬሽን ኃላፊዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው በቀጥታ ወደ ፓሪስ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ የላከችውን ዘገባ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ፡፡
ሃይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ