1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥቁር አሜሪካዊዉን ገድሏል የተባለዉ ፖሊስ የፍርድ ሂደት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 21 2008

በፖሊስ የጥንቃቄ አያያዝ ጉድለት ከስምንት ወራት በፊት ለሞተዉ ጥቁር አሜሪካዊ ፍትህን ያጎናጽፋል የተባለዉ የፍርድ ሂደት ትናንት በሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ቦልቲሞር ላይ ተጀመረ።

https://p.dw.com/p/1HFMy
USA Baltimore Prozess gegen William Porter
ምስል Getty Images/R. Carr

ጥቁር አሜሪካዉያንና ሌሎች በአናሳነት የተፈረጁ ዜጎች ላይ ፖሊስ ያደርጋል የተባለዉን ሕገ-ወጥና አድሎዋዊ አያያዝን አስመልክቶ ፍርድ ቤት ሲታይ በዩኤስ አሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል። በወንጀሉ ሦስት ነጭና ሦስት ጥቁር ፖሊሶች ተጠያቂ መሆናቸዉም ታዉቋል። እንዲያም ሆኖ ስድስቱ ፖሊሶች ተጠያቂ ናቸዉ ቢባልም፣ ለጊዜዉ ትናንት በዝግ ችሎት የቀረቡት አንድ ነጭና አንድ ጥቁር ፖሊስ መሆናቸዉን የዋሽንግተኑ ወኪላችን የላከልን ዝርዝር ዘገባ ያስረዳል።


መክብብ ሸዋ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ