1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጎዞ ዓድዋ 4 «ታሪክን እንዘክራልን» 

ሐሙስ፣ የካቲት 2 2009

«የአድዋ ድል እንደምናዉቀዉ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ መላ ኢትዮጵያን አንድ አድርገዉ በሚያስተባብሩ ጊዜ በሃሳብም በፖለቲካም ልዩነት ያለዉ ወዳጅም ጠላትም ነዉ አንድ ላይ አሰልፈዉ ነዉ ድሉ ሊመጣ የቻለዉ። ስለዚህ በየትኛዉም መንገድ በየትኛዉም ዓይነት ሁኔታ በኢትዮጵያ ነጻነት የሚያምን፤ በኢትዮጵያ ሉዋላዊነት የሚያምን ዓድዋን ይዘክራል።»

https://p.dw.com/p/2XGcL
Äthiopien | Reise zum Gedenktag der Schlacht von Adwa: Guzo Adwa
ምስል Addis Standard/Y. Shumete

ጎዞ ዓድዋ 4 «ታሪክን እንዘክራልን»

ኢትዮጵያዊነትን ለመዘከር አባቶቻችን ለነፃነታችን የከፈሉትን ዋጋ በማሰብ ደግሞ ለትዉልዱ ይህንን መልክት ለማሸጋገር የሚፈልግ ለማንኛዉም ዜጋ ሁልጊዜም ጥሪ እናቀርባለን»   

ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር የተዋደቁ ጀግኖቻችንን የምንዘክርበት፥ በአንድነት፤ በፍቅር፤ በቆራጥነት፤በብልሃትና በታማኝነት ዘምተው ሃገራችንን የነፃነት ምልክት ያደረጉ መሪዎችንና ዘማቾችን ስማቸውን እያነሳን የምንማማርበት፤ ታላቁ የአድዋ ድላችን ዝክር ዘንድሮም ቀጥሏል ሲሉ የ«ጉዞ አድዋ» 4  ተጓዦች ከ25 ቀናት በፊት ከመዲና አዲስ አበባ 1010 ኪሎሚትር ርቀት ላይ ወደሚገኘዉ ወደ አድዋ ጉዞአቸዉን ጀምረዋል።  የ«ጉዞ አድዋ» 4  ዋና አስተባባሪና መስራች ከሆኑት አንዱ አቶ ያሬድ ሹቴን ነበሩ። ዘንድሮ ለ 121 ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የዓድዋን በዓል አድዋ  ላይ ለማክበር ከአዲስ አበባ ጣይቱ ሆቴል የተነሱት ወጣቶች የአገርን ድንበርና ክብርን ጠብቀዉ ያስረከቡን እናትና አባቶች በእግራቸዉ እንደተጓዙ ሁሉ ወጣቶቹም የናት የአባቶቻቸዉን ፈልግ በመከተል በእግራቸዉ የአድዋን ስሜት እየተጋሩ ታሪካቸዉን እያነበቡ እየተማማሩ በደረሱበት ሁሉ የአድዋን ታላቅነት እየነገሩና እየሰበኩ የትዉልድ ግዴታቸዉን ለመወጣት ትጋት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል። በዚህ ዝግጅታችን ከሦስት ቀናት በፊት ዉጫሌን ተሻግረዉ ትናንት ምሽት መርሳ ከተማ ላይ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዉ ዛሬ ሰሜናዊ ወሎን አቋርጠዉ ትግራይ ድንበር ላይ የሚገኙት የጉዞ አድዋ ተጓዦችን ጋብዘን የዓድዋን ታሪክ እንቃኛለን።

Äthiopien | Reise zum Gedenktag der Schlacht von Adwa: Guzo Adwa
ምስል Addis Standard/Y. Shumete

የአድዋ መንፈስ ክብርና ዝና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ አድዋን በስዕል አድዋን በፎቶ ሳይሆን አድዋን እንደ አባቶች አድዋ ላይ የታየውን ታላቅ ኢትዮጵያዊነት ከትውልድ ትውልድ ሳይቋረጥ እንዲተላለፍ የተነሡ ወጣቶች ያዘጋጁት መርሃ-ግብር እነሆ 121 ኛዉን ክብረ በዓል በድምቀት ለማክበር ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ጎዞዉን ጀምሮአል። ይህን ዝግጅት ከመስረት ጀምሮ ከዛሬ አራት ዓመት ጀምሮ ይህን ጉዞ በማስተባበር የሚታወቁት የፊልም ሰራተኛዉ አቶ ያሬድ ሹመቴ ትናንት ምሽት ላይ ያገኘናቸዉ ሰሜናዊ ወሎ መርሳ ከተማ ላይ ነዉ፤ ዓድዋ ለመድረስ ግማሽ መንገድን አጠናቀዋል።    

ተጓዦቹ  እንደ እንደ አድዋ ዘማቾች ወኔ፤ ታሪክን ሃገርን ለማስተዋወቅ ትልቅ ሕልም እንጂ ኃብት የሌላቸዉ ወጣቶች ናቸዉ። በየደረሱበት ከተማ በየደረሱበት የገጠር መንደር ግን ማኅበረሰቡ ጉሮ ወሸባዬ ብሎ ሆ ብሎ ተቀብሎ ምግብ አብልቶ ለስንቅ የሚሆን ቆሎ ቋጥሮም እንደሚሸናቸዉ ተናግረዋል።  

Äthiopien | Reise zum Gedenktag der Schlacht von Adwa: Guzo Adwa
ምስል Addis Standard/Y. Shumete

ከ121 ዓመታት በፊት እንደሆነው ሁሉ በየአካባቢው ተጓዦችን እየተቀበለ በማስተናገድ ላይ ለሚገኘው ጨዋው የሃገራችን ሕዝብ ምስጋናችን ከልብ ነው ሲሉ ገልፀዋል። የጉዞ አድዋ አዘጋጆች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለጉዞ ከመነሳታቸዉ በፊት የሚያስፈልጋቸዉ ነገር ያሟላሉ። ለምሳሌ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በተገኘ የጤና ምርመራ ድጋፍ ተጓዦች ጉዞ ለመጀመር ሙሉ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው፤ አዲስ አበባ እምብርት ላይ ከሚገኘዉ ታሪካዊዉ ጣይቱ ሆቴል ጥር ስምንት ከምሽት ከትመዉ ጥር ዘጠኝ ጉዞአቸዉን ጀምረዋል። በወቅቱ መንግሥት የደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጓዦቹን አላደናቀፈ ይሆን ? ያሬድ ሹመቴ ጉዞ ከመጀመራችን በፊት የሕግ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከፖሊስ ወረቀት አጽፈን ነዉ የምንቀሳቀሰዉ። በርግጥም በዚህ ዓመት ጉዞአችን ለመጀመር ትልቅ ችግር አጋጥሞን ነበር።  

አቶ ያሬድ ሹመቴ እንደጠቀሱት ዘንድሮ እየተካሄደ ባለዉ ጉዞ አድዋ 4 ላይ መብግሥት ከምንም ጊዜ በላይ ድጋፉን አሳይቶአል። በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር  አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደተናገሩት ወጣቶቹ የኢትዮጵያዊ ጀግንነትንና ታሪክ ሰሪነትን ሚና እየደገሙት ነዉ። አቶ ያሬድ ሹመቴ እንደጠቀሱት ዘንድሮ እየተካሄደ ባለዉ ጉዞ አድዋ 4 ላይ መብግሥት ከምንም ጊዜ በላይ ድጋፉን አሳይቶአል። በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር  አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደተናገሩት ወጣቶቹ የኢትዮጵያዊ ጀግንነትንና ታሪክ ሰሪነትን ሚና እየደገሙት ነዉ።

ወጣቶቹ የጀመሩትን ይህን ታላቅ ተግባር በማስፋት ቦታዉን ታዋቂ እናደርገዋለን የሚል ሃሳብ አለኝ ሲሉ በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ አክለዋል።

የጉዞ አድዋ ተጓዦች በጉዞአቸዉ ታሪክን እያነበቡ ታሪካዊ ቦታዎችን እያዩ በፎቶና በፊልም እየቀረፁ ይጓዛሉ። በጉዞ ላይ ከቀረቡት ታሪኮች መካከል በበዓድዋ ጀግንነት የሚታወቁት ቀኛዝማች ታፈሰ አባይነህ ናቸዉ። ቀኛዝማች ታፈሰ በ21 ዓመታቸው ታላላቅ ጀብዱዎችን በመፈፀም የቀኝ አዝማችነትን ማዕረግ የተቀዳጁ ድንቅ ተዋጊ ልጅ እግር ጀብደኛ ሰው መሆናቸዉ ይነገርላቸዋል። በዓድዋው ጦርነት ዋዜማ አምባ አላጌ የጦር አውድማ ላይ በተካሔደው ውጊያ ከበላይ አካል ትዕዛዝ ሳያገኙ ከፊታውራሪ ገበየሁ ጋር በመሆን ውጊያውን ያስጀመሩም ናቸው። እኚሁ ጀግና በዚህ የአይበገር ባይነት፥ ወኔ ባህሪያቸው ተነሳስተው ዓድዋ ላይ በተካሔደው ጦርነት ብዙ ጀብዱ ሰርተው ህይወታቸውን እስከ ማጣት መድረሳቸዉን የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ።   

Äthiopien | Reise zum Gedenktag der Schlacht von Adwa: Guzo Adwa
ምስል Addis Standard/Y. Shumete

 ዛሬ ጉዞ ወደ አድዋ 25ኛ  ቀናቸዉ ላይ የሚገኙት ዋና አስተባባሪ አቶ ያሬድ ሹመቴ  የአድዋ ድል ሲሉ በሰፊዉ የታሪክ ማብራርያን ሰጥተዋል። «የአድዋ ድል እንደምናዉቀዉ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ መላ ኢትዮጵያን አንድ አድርገዉ በሚያስተባብሩ ጊዜ በሃሳብም በፖለቲካም ልዩነt ያለዉ ወዳጅም ጠላትምም ነዉ አንድ ላይ አሰልፈዉ ነዉ ድሉ ሊመጣ የቻለዉ ስለዚህ በየትኛዉም መንገድ በየትኛዉም ዓይነት ሁኔታ በኢትዮጵያ ነጻነት የሚያምን በኢትዮጵያ ሉዋላዊነት የሚያምን ፤ ኢትዮጵያዊነትን ደግሞ ለመዘከር አባቶቻችን ለነፃነታችን የከፈሉትን ዋጋ በማሰብ ደግሞ ለትዉልዱ ይህንን መልክት ለማሸጋገር የሚፈልግ ማንኛዉም አካል ሁልጊዜም ጥሪ እናቀርባለን»   

በኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የመዳረሻ ቦታዎች ልማት ዳይሬክተር አቶ ቸርነት ጥላሁን እንደገለፁት፤ የጉዞ አድዋን ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን የዓለም ሃገራት ሃገር ጎብኝዎች እንዲካፈሉበት ጥረት እያደረግን ነዉ። 

ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን የጉዞ አደዋ  መንገድ ባለፉት ጊዜያት በእግራቸዉ አቆራርጠዉ እንደ እቴጌ ጣይቱ አድዋ ላይ ሰንደቃቸዉን የተከሉ ወደ ሦስት የሚሆኑ ሴቶች ይገኛሉ። በዘንድሮዉም ጉዞ ላይ ሁለት ሴቶች ተካፋይ ናቸዉ። በዓድዋ ጦርነት  በጣም ከፍተኛ ቦታ ይሰጣቸዉ ከነበረ የጦር አዛዥ መካከል የጦር አዛዥ ወልደፃድቅ የሚባሉት የቅም አያቱን ታሪክ ለመዘከር በጉዞዉ ላይ የተሳተፈዉ ወጣት ያሬድ እሸቱ ይባላል።

በማስታወሻ ደብተራቸዉ ተሞክሮአቸዉን እየፃፉ መንገዱ ተጋምሶአል ይላሉ፤ ጉዞ አድዋ 4 ተጓዦች። ታዲያ ዘንድሮ ወደ አድዋ ጉዞ ከጀመሩት ሁለት ሴቶች መካከል  ረዚና እቁባሚካኤል ለረዥም ግዜ ውሀ ቋጥሮ የነበረው የቀኝ እግሯ ወለል አላራምዳት በማለቱ ተጓዦች  እስከ መርሳ ከተማ መግቢያ ድረስ በቅብብሎሽ በሽኮኮ በፈረስ ተቅመዉ አድርሰዋታል። እንግዳ ተቀባዮቹ የመርሳ ወጣቶችም ከተጓዦች በመቀበል እስከ ማረፊያ ቦታ ድረስ አንከብክበው በማድረስ እገዛ ማድረጋቸዉን ተጓዦች ገልፀዋል። የመርሳ ከተማ ባህል ቡድን ደማቅ አቀባበል እና ልዩ የሙዚቃ ትርኢት ሲቀርብ አምሽቶ ተጓዦች የደከመ ሰውነታቸውን በባህላዊ ሙዚቃዎች በመነቃቃት የደስታ ግዜም ማሳለፋቸዉን ተጓዦቹ በማስታወሻቸዉ ከትበዋል።

Äthiopien | Reise zum Gedenktag der Schlacht von Adwa: Guzo Adwa
ምስል Addis Standard/Y. Shumete

ደሴ ከንጉስ ሚካኤል አይጠየፍ ደጃፍ፤ ከአዲስ አበባ 350 ኪ.ሜ ርቀት ገደማ የምትገኘው የሀርቡ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ አድረዋል። ከከሚሴ ከተማ ወደ ሀርቡ በሚጠጉበት ግዜ ፍንጭቱ ከተባለች ፏፏቴ ስር  እረፍትም ወስደዋል።

በር ከተማ ተነጣጥለው የደረሱበትን ክስተት ማስተናገዳቸዉን በጉዞ ማስታወሻቸዉ አስፍረዋል። ወደ ሃያ ሁለት ቀናት ግድም የቀራቸቸዉ የጉዞ አድዋ 4 ተጓዞች አድዋ ደርሰዉ 121ኛዉን የአድዋ ደርሰዉ እንደቀደምቱ አባት እናቶቻች  ቦታዉ ላይ ባንዲራቸዉን ተክለዉ በዓሉን በድምቀት ሲያከብሩ ዳግም ታሪካቸዉን ሊነግሩን እቅድ ይዘዋል። ቀደም ብለን እንደጠቀስነዉ ወጣቶቹ ይህን ጉዞ ሲያደርጉ ታሪክን እያነበቡ የራሳቸዉን ታሪክ ደግሞ ለተኪዉ ትዉልድ ለማስተላለፍ በፎቶ እያስደገፉ እየጻፉ ነዉ። ይበል ብለናል! ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ