1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብፅ የዉኃ አጠቃቀምን አስመልክቶ ማዕቀፉ እንዲሻሻል ዳግም ሃሳብ አቅርባለች።

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ግንቦት 10 2009

የዓባይ ዉሃ ፍትሃዊ አጠቃቀምን ያስከብራል የተባለ «የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ» ህጋዊ ሰነድ እስካሁን በስድስት ሀገሮች ተፈርሞ፤ በሦስቱ ፀድቋል። ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠችዉ ግብፅ እስካሁን ማዕቀፉን ሳትፈርም የቆየች ሲሆን ከወራቶች ወዲህ ጀምሮ ደግሞ የዉኃ አጠቃቀም መብቷን አስመልክቶ ማዕቀፉ እንዲሻሻል ዳግም ሃሳብ አቅርባለች።

https://p.dw.com/p/2dC5b
Sudan Khartum Abkommen gemeinsame Nil-Wasser Nutzung
ምስል AP Photo/Mohammed Abd el-Moaty, Egyptian Presidency

Ethiopia Refute Egypt's Rights Demand on Nile - MP3-Stereo

ከሰባት ዓመት በፊት የረቀቀዉ የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ አንቀጽ 14(b) ስር የዓባይ ዉኃን የአባል አገሮቹን የዉኃ ደንነትን በጣም ሳይጎዱ መጠቀም እንዲችሉ ያሳስባል። በግዜዉ በዚህ አንቀፅ ላይ ያልተስማሙት ግብፅና ሱዳን እንደነበሩ ማዕቀፉ ያሳያል። ግብፅም የዉኃ ደንነቷ እንዲጠበቅላት አሁን ያለዉን የዉኃ መጠን በማያዉክና በዉኃዉ ላይ ያላት መብት በሚጠበቅላት መልክ ይህ አንቀፅ እንዲተካ ሃሳብ አቅርባ እንደነበረበም ይህ ህጋዊ ሰነድ ይጠቁማል።

ይህን ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠችዉ ግብፅ እስካሁን ማዕቀፉን ሳትፈርም የቆየች ሲሆን ከወራቶች ወዲህ ጀምሮ ግን ስለ ዉኃ መብቷን አስመልክቶ ማዕቀፉ እንዲሻሻል ዳግም ሃሳብ ማቅረቧ ለመረዳት ተችለዋል። የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለም ሰሞኑን የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡም ኢትዮጵያ ጥያቄዉን እንደማትቀበል መናገራቸዉ የአገር ዉስጥ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ግብጽ በሰነዱ ላይ ለመወያያት ፍላጎት ማሳየቷንና ስላቀረበችዉ ጥያቄ በተመለከተ በሚንስትሩ መስርያ ቤት የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብዙነህ ቶልቻ እንዲ ስሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በሃይድሮ ፖለቲክስ ማለት በዉኃ አጠቃቀም ዙርያ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ያቆብ አርሳኖ  የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በድርድሩ ላይ ለመስማማት የሄዱበት ረጅም ረቀት በቅርበት ስከታተል የአንቀፁ መቀየር «አስፈላግም፣ ተገቢም» አይደልም ሲሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ግብጽ ጥያቄዉን ለመጠየቅ መብት አላት የሚሉት ዶክተር ያቆብ፣ ግን ጥያቄዉ ፍታዊ አለመሆኑንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ በምትገነባዉ ግድብ የግብፅና የሱዳንን የዉኃ ደህነት እንዳይጎዳ ቴክንካዊ ጥናት ለሁለት ፈረንሳይ ኩባንያ መሰጠቱ ይታወሳል። አርቴሊያ እና «BRL» የተሰኙት ኩባንያዎቹም ስራቸዉን  በየካትት ወር 2009 መጀመራቸዉን አቶ ብዙነህ ይናገራሉ። 

መርጋ ዮናስ
ነጋሽ መሐመድ