1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕዝበ ውሳኔው የድርድሩ ማብቂያ እንዳይሆን ያሰጋል

ማንተጋፍቶት ስለሺቅዳሜ፣ ሰኔ 20 2007

የዩሮ ዞን የገንዘብ ሚኒስትሮች ግሪክን ከገንዘብ ቀውስ ለማውጣት የግሪክ መንግሥት እንዲራዘምለት ያቀረበውን የተጨማሪ መርሐ-ግብር ጥያቄ ቅዳሜ ውድቅ አደረጉ። መርሐ-ግብሩ ማክሰኞ ምሽት ላይ አገልግሎቱ ያከትማል ተብሏል። የግሪክ መንግሥት የአውሮጳ ሕብረት የቁጠባ መረሃ ግብርን አስመልክቶ ህዝበ-ውሳኔ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

https://p.dw.com/p/1FoT7
Brüssel Treffen der Finanzminister Beratung Griechenland
ምስል Reuters/Y. Herman

በግሪክ የቁጠባ መረሃ ግብር ላይ ለመወያየት ዛሬ ብራስልስ የተሰበሰቡት የዩሮ አባል ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች የግሪክ ብድር ከመጪው ማክሰኞ በኋላ እንደማይራዘም አስታወቁ። ሚኒስትሮቹ ከመሰብሰባቸው አስቀድሞ ሌሊቱን የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ የአውሮፓ ህብረት ያቀረበውን የቁጠባ መረሃ ግብር አስመልክቶ በግሪክ ሰኔ 28 ቀን ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ጠርቶው ነበር። በዚህም የተነሳ ማክሰኞ የሚያበቃው የብድር ቀነ ቀጠሮ ግሪክ አበዳሪዎቿ ለተወሰኑ ቀናት እንዲያራዝሙላት ጠይቃለች። አበዳሪዎቹ የሲፕራስን የህዝበ ውሳኔ ሀሳብ በጥብቅ አውግዘዋል።

ልደት አበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ