1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አወዛጋቢዉ የጉዞ እገዳ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 12 2010

የተመሰረተበትን የወርቅ እዮቢልዩ ማለት 50ኛ ዓመት መታሰብያ ነገ ለማክበር ዝግጅት ላይ ያለዉ በኔዘርላንድ የሚገኘዉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል  በክብር እንግድነት የጋበዘዉ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብት ተከራካሪዉ እስክንድር ነጋ ከጉዞ መታገዱ እንዳሳዘነዉ ገለፀ።

https://p.dw.com/p/2wPlc
Äthiopien Kaliti Gefängnis
ምስል Befekadu Hailu

«መሄድ ትችላለሁ ተብዬ ፓስፖርቴ ተሰቶኛል» እስክንድር ነጋ

ነገ አምስተርዳም ላይ በሚካሄደዉ ክብረ በዓል ላይ የኔዘርላንዱን ንጉስ ቪለም አልክሳንደርን ጨምሮ የሃገሪቱ ባለሥልጣናትና የድርጅቱ ተጠሪዎች እንደሚገኙበት ተነግሮአል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት አዲስ አበባ ላይ በስልክ ያገኘነዉ ጋዜጠኛና የመብት ተቆርቋሪዉ እስክንድር ነጋ ትናንት ምሽት ጉዞዉን ሲታገድ የተነጠቀዉ ፓስፖርቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ እንደተመለሰለት ተናግሮአል። መጓዝም እንደሚችል ተነግሮኛል ብሎአል።  ጋዜጠኛ እስክንድር ትናንት አዉሮፕላን ማረፍያ ያጋጠመዉን በመዘርዘር ይጀምራል።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ