1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

jጄኮብ ዙማ እና የደቡብ አፍሪቃ ውሳኔ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 3 2009

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ  ትናንት ኬፕታውን በሚገኘው ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በሚስጥር የተካሄድባቸውን የመተማማኛ ድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርዓት ተቋቋሙ። ከ400 እንደራሴዎች መካከል የመተማመኛው ድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የተሳተፉት 384 ብቻ ነበሩ።

https://p.dw.com/p/2hwQp
Südafrika Präsident Zuma übersteht erneut Misstrauensantrag
ምስል Reuters/M. Hutchings

ጄኮብ ዙማ

ፕሬዚደንት ዙማን በሙስና የሚወቅሱዋቸው ተቃዋሚዎች ርዕሰ ብሔሩን ከስልጣን ለማውረድ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተካሄደውን የመተማመኛ ድምፅ 177 እንደራሴዎች ብቻ ደግፈውታል። ዘጠኝ እንደራሴዎች ድምፃቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። የመተማመኛው ድምፅ ያልፍ ዘንድ ከ400 የምክር ቤት እንደራሴዎች መካከ የ201 ድምፅ ያስፈልገው ነበር።

መላኩ አየለ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ